በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፈለገና ኬረን ለኢትዮጵያ የትራፊክ ችግር መላ እየመቱ ነው

ከላይ ፎቶግራፋቸውን የምትመለከቷቸው የ18 ዓመቱ ፈለገ ገብሩ (በስተቀኝ የመጨረሻው)እና የ17 ዓመቷ ኬረን ፋን (በስተግራ የመጀመሪያዋ) አዲስ አበባ ውስጥ የትራፊኩን እንቅስቃሴ እየቀረቡ ያሉ ወይም እያቋረጡ ያሉ እግረኞችን ለአሽከራካሪዎች ቀድሞ የሚጠቁምና ማስጠንቀቂያ የሚሰጥ ሥርዓት ነድፈዋል፡፡

ኢትዮጵያ በዓለም በመንገድ ላይ በሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች ሣቢያ በእግረኛ ላይ በሚደርስ የሞት መጠን በዓለም ከቀዳሚዎቹ መካከል እንደሆነች ይነገራል፡፡

ከላይ ፎቶግራፋቸውን የምትመለከቷቸው የ18 ዓመቱ ፈለገ ገብሩ (በስተቀኝ የመጨረሻው)እና የ17 ዓመቷ ኬረን ፋን (በስተግራ የመጀመሪያዋ) አዲስ አበባ ውስጥ የትራፊኩን እንቅስቃሴ እየቀረቡ ያሉ ወይም እያቋረጡ ያሉ እግረኞችን ለአሽከራካሪዎች ቀድሞ የሚጠቁምና ማስጠንቀቂያ የሚሰጥ ሥርዓት ነድፈዋል፡፡

ይህ ሥርዓት ሁለቱንም የመንገዱን ተጠቃሚዎች፤ እግረኛውንም አሽከርካሪውንም በተጨናነቁ መንገዶች ላይ ደኅንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ መንቀሣቀስ እንዲችሉ ያግዛል የተባለለት ፈጠራ ነው፡፡
የእነ ፈለገ የፈጠራ ቡድን በዋይት ሃውሱ የሣይንስ ፌስቲቫል ላይ
የእነ ፈለገ የፈጠራ ቡድን በዋይት ሃውሱ የሣይንስ ፌስቲቫል ላይ
መሣሪያው በፀሐይ ኃይል በሚሞላ ባትሪ የሚንቀሣቀስ ሲሆን እየመጡ ወይም እየቀረቡ ያሉ ተሽከርካሪዎች ማቋረጫ ወይም እግረኞች ባሉባቸው አካባቢዎች የሚደርሱበትን ጊዜ እያሰላ የሚሠራ ባለሁለት ወይም መንታ መቃኛ ዘዴ ያለው ነው፡፡

ፈለገ እና ካረን የኒውሰን ኖርዝ ከፍተኛ ትምህርት ቤት “የፈጠራ ቡድን” መሪዎች ናቸው፡፡ በየዓመቱ ለትርዒት ለሚቀርበው ዩሬካ ፌስቲቫል እንዲህ ዓይነት መፍትሔ አዘል ሃሣቦች ያሉባቸውን አነስተኛ የፈጠራ ማሳያዎች ይሠራሉ፤ ያሰናዳሉ፡፡

ሁለቱም፤ ፈለገም ኬረንም አሜሪካዊያን ይሁኑ እንጂ የተወለዱት አሜሪካ ውስጥ አይደለም፡፡ ፈለገ በብራውን ዩኒቨርሲቲ የኮምፕዩተር ሣይንስ እና የቪዥዋል አርትስ የአንደኛ ዓመት ተማሪ ነው፡፡

ኬረን ደግሞ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪና የትምህርት ቤቷ የባድሜንተን ቡድን አምበል ነች፡፡
XS
SM
MD
LG