በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ካንሠር ደኆችን እያሠጋ ነው - ጥር 27 የዓለም የካንሠር ቀን


ጥር 27 የዓለም የካንሠር ቀን

ከካንሰር አጠቃላይ የሞት መጠን አንድ ሦስተኛ የሚሆነው ለመከላከልና ለማስቀረት የሚቻል መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:58 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


ከካንሰር አጠቃላይ የሞት መጠን አንድ ሦስተኛ የሚሆነው ለመከላከልና ለማስቀረት የሚቻል መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡ ይሁን እንጂ ከዓለም ሃገሮች ግማሽ የሚሆኑት ሕይወት አድን የሆነ የካንሠር መከላከያና መቆጣጠርያ መርኃግብር እንደሌላቸው ይኸው የጤና ድርጅቱ ሪፖርት ገልጿል፡፡

ካንሰር በዓለም ዙሪያ ግንባር ቀደም የሚባል ገዳይ የጤና ችግር በመሆኑ ሃገሮች ለዚህ ችግር ትኩረት እንዲሰጡ፣ ለመካላከል ለመቆጣጠር የሚያስችሉ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ለማስታወስና ለማገዝ ሲባል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥር 27 ወይም ፌብርዋሪ 4 ቀን የዓለም ካንሠርን የመዋጋት ቀን ሆኖ እንዲውል ወስኗል፡፡ በዚህ ዕለት በተጓዳኝም ስለካንሰር የተሣሣቱ ግንዛቤዎችንም ለማስወገድ ቅስቀሣዎች ይደረጋሉ፣ ትምህርቶች ይሰጣሉ፡፡
ጥር 27 የዓለም የካንሠር ቀን
ጥር 27 የዓለም የካንሠር ቀን

በአውሮፓ የዘመን አቆጣጠር በ2008 ዓ.ም ውስጥ ብቻ በዓለም 7.6 ሚሊየን ሰው በካንሰር ምክንያት መሞቱንና በየዓመቱም አሥራ ሦስት ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች ለአዳዲስ የካንሠር ሕመሞች እንደሚጋለጡ የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ እንደሚለው ከአዳዲሶቹ ለካንሰር የመጋለጥ አጋጣሚዎች ከሁለት ሦስተኛ በላይ የሚሆነው የሚከሰተው በልማት ወደኋላ በቀሩ ወይም ገና በመልማት ላይ ባሉ ሃገሮች ውስጥ ሲሆን አስደንናገጭ ነው ባለው ሁኔታም እየተስፋፋ ነው፡፡

በዓለም የጤና ድርጅት ሥር የሰደዱ ወይም ነዋሪ ሕመሞች እና የጤና ማስፋፊያ መምሪያ የጤና ጉዳዮች ኃላፊው አንድሪያስ ኢልሪች መጭው ጊዜ አሣዘኝ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡

ይሁን እንጂ ካንሠር የግድ የሞት ፍርድ ተደርጎ መወሰድ የለበትም፤ ሰዎች እንደትምባሆ እና አልኮኾል ከመሣሰሉት ጎጂ አቅርቦቶች እራሣቸውን ካራቁ፤ የአመጋገባቸውን ሁኔታ ካስተካከሉ፤ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ካደረጉና ለአኗኗራቸው ሁኔታ ተገቢውን ትኩረት ከሰጡ ከአጠቃላዩ ለካንሠር የመጋለጥ አጋጣሚና ከተጋለጡም የሞት መጠኑን እስከ አንድ ሦስተኛ መቀነስ እንደሚችሉ የጤና ድርጅቱ ይናገራል፡፡

ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ፡፡

አስተያየቶችን ይዩ (3)

XS
SM
MD
LG