በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተሻሻለ የኮቪድ-19 ክትባት ሊዘጋጅ እንደሚችል ተጠቆመ


የምግብ እና መድኃኒት አስተዳደር
የምግብ እና መድኃኒት አስተዳደር

በአገልግሎት ላይ ያለው የኮቪድ-19 ክትባት፣ ልውጡን የኦሚክሮን ቫይረስ ለመዋጋት በሚያስችል መልኩ ጎልብቶ፣ በመጪው የፈረንጆች የመኸር ወቅት ሊቀርብ እንደሚችል ተጠቁሟል።

አሁን በመሰጠት ላይ ያለው ክትባት፣ መጀመሪያ ለታየው የኮሮና ቫይረስ ዐይነት የተዘጋጀ ቢኾንም፣ በሒደት ተሐዋሲው ባሕርይውን ሲቀይር፣ ክትባቱም በትይዩ እየተቀየረ ቆይቷል።

ዐዲሱ ክትባት፣ ልውጡን የኦሚክሮን ዝርያ ብቻ ዒላማ ማድረግ ይኖርበት እንደኹ፣ የአሜሪካው የምግብ እና መድኃኒት አስተዳደር ሳይንቲስቶች እየተማከሩ ናቸው።

የወረርሽኙ ሥርጭት እየቀነሰ ቢኾንም፣ ክረምቱ ሲገባ ሊባባስ ይችላል፤ የሚል ስጋት እንዳላቸው፣ የአስተዳደሩ የክትባት ሓላፊ ዶር. ፒተር ማርስ ተናግረዋል።

የምግብ እና መድኃኒት አስተዳደሩ፣ አሜሪካውያን በየዓመቱ፣ ዐዲስ ዓይነት የኢንፍሉዌንዛ ክትባት እንደሚቀርብላቸው ሁሉ፣ በመጪው ክረምትም፣ ለተሻሻለ ዐዲስ የኮሮና ክትባት እንዲዘጋጁ መልዕክቱን አስተላልፏል።

XS
SM
MD
LG