ደሴ —
ፌስቡክ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ያወጡትን ጹሑፍ ማንሳቱን አስታወቀ። “
ፌስቡክ ያነሳው ጠላታችንን በደማችን እንቀብራለን” የሚለውን እና “አሸባሪ” ካሉት ኃይል አገራቸውን ለመከላከል ዜጎች እንዲነሱ ጥሪ የሚያደርገውን ንግግራቸውን ነው።
በሃምሊን ዩኒቨርስቲ ኮሙዩኒኬሽን ትምሕርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር እንዳልካቸው ጫላ፤ “ጹሑፉ የተነሳው በጫና ምክንያት ነው”ይላሉ።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ