በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ እና በደቡብ ክልል ገበሬዎች ተፈናቀሉ


የአማራ ክልላዊ መንግሥት ምላሽ ሰጥቷል

በአማራ ክልል በባህርዳር ከተማ ይባብ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ይኖሩ የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ አባወራ ቤቶች ሕገ ወጥ ግንባታ ናችሁ በሚል እንደፈረሱ ተጎጂዎች ተናገሩ።

በዚህ ምክንያት በተፈጠረ ግጭት ብዙ ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች እንደተደበደቡና አንድ ሰውም በደረሰበት ጉዳት ወደ ሆስፒታል መወሰዱ ታውቋል።

በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን ማርቃ ወረዳ ለከተማ ማስፋፋያ በሚል ከ180 በላይ የሚሆኑ የአባወራ ቤቶች በኃይል እንደፈረሱም የጉዳቱ ሰለባዎች ለቪኦኤ ገልፀዋል።

በሁለቱም ክልሎች ከዚህ ጋር ተያይዞ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎች ለእስር ተዳርገዋል የአማራ ክልል ቃል አቀባይ በበኩላቸው ሕገወጥ የተባሉ ቤቶች መፍረሳቸውን ገልፀው ተፍፅሟል የተባለው ድብደባ ስለመድረሱ ግን መረጃ እንደሌላቸው አስታውቀዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በአማራ እና በደቡብ ክልል ገበሬዎች ተፈናቀሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:54 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG