በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የኢትዮጵያ ክፍሎች የረሃብ ስጋት አለ


በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የኢትዮጵያ ክፍሎች የረሃብ ስጋት አለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:08 0:00

በኢትዮጵያ ስድስት ተከታታይ ወቅት ዝናብ ላይጥል እንደሚችል በመገመቱ በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የኢትዮጵያ ክፍሎች ለረሃብ አደጋ ሊጋለጥ ይችላል ሲል አክሽን አጌንስት ሀንገር የተሰኘው በአፍሪካ ቀንድ ረሃብን ለማጥፋት የሚንቀሳቀሰው ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ርዳታ ሰጪ ተቋም አስጠነቀቀ።

በኢትዮጵያ እስካሁን ቢያንስ 12 ሚሊየን ሰዎች ለሞት ለሚዳርግ የድርቅ አደጋ መጋለጣቸውን እና ከ4.5 ሚሊየን በላይ የቀንድ ከብቶች መሞታቸውን የተቋሙ የኢትዮጵያ ፕሮግራም ዳይሬክተር ቤዛ አበበ ተናግረዋል።

ለከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት የተጋለጡ ህፃናት ቁጥርም በከፍተኛ ሁኔታ እየጨምረ መሄዱን ዳይሬክተሯ ጨምረው ተናግረዋል። በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለው የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ በቀጠናው እየከፋ የሄደውን ድርቅ ለመቅረፍ ቅድሚያ ሰጥቶ እንዲወያይም ጠይቀዋል።

XS
SM
MD
LG