በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመሰደድ ምክንያቶች በኢትዮጵያዊያን ምሁራን ጥናት


ፕሮፌሰር ሰዒድ ሃሰን እና ፕሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽ
ፕሮፌሰር ሰዒድ ሃሰን እና ፕሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽ

ሁለት ኢትዮጵያዊያን የምጣኔ ሃብት ምሁራን በአውሮፓ አቆጣጣር በታኅሳስ 2013 ዓ.ም ኢትዮጵያዊያንን ከአገር በሚያስኮበልሉ ምክንያቶች ላይ የምርምር ሪፖርት አቅርበዋል።

please wait

No media source currently available

0:00 0:31:22 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ሁለት ኢትዮጵያዊያን የምጣኔ ሃብት ምሁራን በአውሮፓ አቆጣጣር በታኅሳስ 2013 ዓ.ም ኢትዮጵያዊያንን ከአገር በሚያስኮበልሉ ምክንያቶች ላይ የምርምር ሪፖርት አቅርበዋል።

ምሁራኑ ምክንያቶቹን በሦስት አበይት ክፍሎች አስቀምጠዋቸዋል። አንደኛ፣ ወጣቶቹ ከአገር እንዲወጡ ከውስጥ የሚገፉ፤ ሁለተኛ፣ ከውጭ የሚስቡ ወይም የሚያማልሉና ሦስተኛ፣ ተባባሪ በመሆን የመሰደድ ፍላጎትን የሚያመቻቹ ሁኔታዎች ብለው ነው የተነተኗቸው፡፡

ወጣቶችን ካገር ለመሰደድ ከሚገፉ ሁኔታዎች መካከል የሥራ ዕድል ማጣት፣ የመልካም አስተዳደር መጥፋትና ሙስና እንደ አብይ ምሳሌዎች ተጠቅሰዋል።

አነስ ባለ ደረጃ ከአገር ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ገንዘብ ወደ አገር በመላክ በቤተሰብ ኑሮ ላይ የሚያደርጉት አዎንታዊ ለውጥ እንደ አንድ ማራኪ ሁኔታ የተጠቀሰ ሲሆን በተጓዳኝ የወጣቶችን በቀላሉ ከአገር መውጣት የሚያመቻቹ ሁኔታዎች ግን ዋናዎቹ ጎጂ ሁኔታዎች መሆናቸውን ምሁራኑ በጥናታቸው ተንትነዋል።

በአብይነት ከተጠቀሱት መካከል መንግሥት የውጭ ምንዛሪ ካዝናውን ለማካበት ዜጎች በገፍ በመሰደድ ለአደጋ እንዲጋለጡ አድርጓል የሚል ይገኝበታል፡፡

በአገር ውስጥ የህጋዊና ሕገወጥ ደላላዎችን መብዛት በመጥቀስ አጥኚዎቹ “ምናልባት ከአንዳንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ጋር ቁርኝት ሊኖራቸው እንደሚችል” ምክንያታዊ በሆነ ትንተና አስረድተዋል።

ሜዲቴራኔያን ባሕር፤ የላምፔዱሳ ሰለባዎች
ሜዲቴራኔያን ባሕር፤ የላምፔዱሳ ሰለባዎች

በጥናቱ እንደ መፍትሔ የተጠቀሱት ወጣቱ የአገሩ ባለቤትነት እንዲሰማው እኩል እና ፍትሃዊ የሥራ ዕድል የአገሪቱን ኢኮኖሚ ውስን በሆኑ ሦስት የሥራ ዘርፎች ማለትም በመንግሥት ከፍተኛ ቀጣሪነት፣ በጥቃቅን ችርቻሮና በእርሻ አንቆ ከመያዝ ይልቅ ሰፊ የሥራ ዕድል ወደሚፈጥር ሰፊ የግል ኢንዱስትሪ ምሥረታ ማሸጋገርን መክረዋል።

አጥኚዎቹ ፕሮፌሰር ሰዒድ ሃሰን፤ በመሪ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ኃብት መምህር፤ እንዲሁም በዴንቨር ሜትሮፖሊታን የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ እና በጆሃንስበርግ ዊትዋተርስታንድ ዩኒቨርሲቲ የሂሣብ አያያዝ ፕሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽ ናቸው።

ምሁራኑ ከትዝታ በላቸው ላይደረጉት ሙሉ ውይይት የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG