በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደሮች ፕሬዚዳንት ትረምፕ ስለአፍሪካ በተናገሩት


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

በአፍሪካ ሃገሮች ተመድበው የሰሩ አርባ ስምንት የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደሮች ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ስለአፍሪካ ሃገሮች አሉ የተባለው ጸያፍ ቃል በጥልቅ አሳስቦናል በማለት ለዋይት ኃውስ ደብዳቤ ልከዋል።

በአፍሪካ ሃገሮች ተመድበው የሰሩ አርባ ስምንት የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደሮች ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ስለአፍሪካ ሃገሮች አሉ የተባለው ጸያፍ ቃል በጥልቅ አሳስቦናል በማለት ለዋይት ኃውስ ደብዳቤ ልከዋል።

አምባሳደሮቹ በደብዳቤያቸው

“እኛ በአርባ ሥምንት የአፍሪካ ሀገሮች ያገለገልን አምባሳደሮች እርስዎ ስለአፍሪካ ሃገሮች በቅርቡ የተናገሩት ነገር በጥልቅ እንዳሳሰበን ከሃምሳ አራቱ የአፍሪካ ሃገሮች ከአብዛኞቹ ጋር ያለን አጋርነት ትልቅ ቦታ ያለው መሆኑን ልንመሰክር እንፈልጋለን” ብለዋል።

እንደአሜሪካ አምባሳደር አፍሪካ ያላትን የተለያየ የከበረ ባህላዊ ፀጋ የሕዝቧን ድንቅ ጥንካሬ እና ደግነት የተመለከትን ነን ብለዋል።

የአህጉሪቱን የንግድ ፈጣሪዎች የኪነ ጥበብ ሰዎች ታጋዮች የተፈጥሮ አካባቢያዊ ጥበቃ ተሙዋጋቾችና መምህራን እናደንቃለን ያሉት የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደሮች ዩናይትድ ስቴትስ ከአፍሪካ ሃገሮች ጋር ያላትን መልካም ግንኙነት ይዛ መቆየት እንደሚያስፈልጋት አጥብቀው አስገንዝበዋል።

አስከትለውም የቀድሞዎቹ አምባሳደሮች ስለአፍሪካና ስለዜጎችዋ ያለዎትን አስተያየት መልሰው እንደሚገመግሙ አፍሪካውያንና አፍሪካውያን አሜሪካውያን ለሃገራችንና ለታሪካችን ላበረከቱትንና ለሚያበረክቱት ታላቅ አስተዋፅዕ እንዲሁም ለዩናይትድ ስቴትስና አፍሪካ ዘላቂ ትሥሥር ዕውቅና ይሰጣሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን ሲሉ በደብዳቤያቸው ገልፀዋል።

ፕሬዚዳንት ትረምፕ ባለፈው ሳምንት ሃሙስ በዋይት ኃውስ ጽኅፈት ቤታቸው ስለኢሚግሬሽን በተካሄደ ስብስባ ላይ ነው ከሄይቲ ከኤል ሳልቫዶር እና ከአፍሪካ የሚመጡትን ስደተኞች ፀያፍ ቃል ተጠቅመው “ከቆሻሻ ሃገሮች የሚመጡት” እንዳሉ ነው የተዘገበው።

በስብሰባው ላይ የነበሩ አንዳንዶች እንዳሉት ፕሬዚዳንቱ

“ከተጠቀሱት ሃገሮች ከምናመጣ ለምን እንደኖርዌይ ካሉት አናመጣም” ብለዋል። ሂይቲን በኢሚግሬሽን ጉዳይ በምናደርገው ሥምምነት ሂይቲ እንዳትገባ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል ተብሏል። ፕሬዚዳንቱ ባለፈው ዕሁድ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል

“እኔ ዘረኛ አይደለሁም፣ እንደኔ ከዘረኝነት የራቀ ሰው አነጋግራችሁ አታውቁም” በማለት አስተባብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG