በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ እና የአውሮፓ ህብረቶች ጉባኤ ከጸረ ኮቪድ ክትባት እስከ ጸጥታ እና የደህንነት ጉዳዮች


ታዳጊው በዲፕስሉት ከተማ በጆሃንስበርግ አቅራቢያ በምትገኝ ሥፍራ የኮቪድ-19 ክትባት ሲሰጠው፤ እአአ ኦክቶበር 21/ 2021
ታዳጊው በዲፕስሉት ከተማ በጆሃንስበርግ አቅራቢያ በምትገኝ ሥፍራ የኮቪድ-19 ክትባት ሲሰጠው፤ እአአ ኦክቶበር 21/ 2021

ቁጥራቸው ደርዘን የሚጠጋ የአፍሪካ መሪዎች ለሁለት ቀናት ለሚዘልቀው የአውሮፓ ህብረት እና የአፍሪካ ህብረት መሪዎች ጉባኤ ወደ ብራስልስ ሲያመሩ፣ “አረንጓዴ ኢንቨስትመንት” የሚል ሥያሜ በተሰጣቸው የተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃን በሚያጎለብቱ የሥራ ዘርፎች ላይ የሚደረግ የመዋዕለ ንዋይ ፍሰትን፣ ፍልሰት እና ስደት፣ የጸጥታ እና የደህንነት ጉዳዮችን፤ እንዲሁም ኢፍትሃዊ የክትባት ሥርጭትን የሚመለከቱ ርዕሶችን ዋና ትኩረት አድርገው እንደሚመክሩ ተዘገበ።

ሰባ በመቶ የሚሆነው የአውሮፓ ነዋሪ ቢያንስ አንድ ዙር የጸረ-ኮቪድ ክትባት የተከተበ ሲሆን፣ ያ አሃዝ በአፍሪካ ሲታይ ግን 16 በመቶ ብቻ ነው። የተዛባው የክትባት ሽፋን ከጉባኤው ቀዳሚ አጀንዳዎች ውስጥ አንዱ ነው።

ክትባቶችን መለገስ አንድ ነገር ነው። ነገር ግን ሰዎች መከተባቸውን ማረጋገጥ ራሱን የቻለ ሌላ። በመሆኑም ፍትሃዊነት ከመለገስም በላይ ማድረግን ይጠይቃል። መሠረታዊ የአሰራር ለውጥ ለውጥ እና የሕክምና ዶክተሮችን፣ ነርሶችን፣ የሆስፒታል አገልግሎትን፣ የህክምና ቁሳቁሶችን መኖር፣ የምርምር እና የተመራማሪዎችን የሥራ ፍሬ እና እንዲሁም ቴክኖሎጂዎችን የመጠቀም ዕድል ማግኘትን ይጠይቃል።

በመጨረሻም ክትባቶችን በአህጉሪቱ ውስጥ ማምረት የሚያስችል አቅም መኖር ከቀደሙት በማይተናነስ ደረጃ አስፈላጊ ጉዳይ ነው” ያሉት ስቴላ ክሪያኪደስ የአውሮፓ የጤና እና የምግብ ደህንነት ጉዳዮች ኮምሽነር ናቸው፣ በቅርቡ በፈረንሳይዋ ሊዮን የተካሄደውን የአውሮፓ ህብረት የጤና ጉባኤ ተከትሎ በሰጡት አስተያየት።

በሌላ በኩል በተለይ አገረ መንግሥት መሰረት የሚዋቀርባቸው ተቋማት ሥር የሰደደ ደካማነት አንዱ መሆኑ የሚታመነው እና በተለይ ምዕራብ አፍሪቃ አገሮች በደጋጋሚ የሚታየው የመንግሥትን ግልበጣ ጉዳይ ትከረት ሰጥተው ከሚወያዩባቸው የጉባኤው አጀንዳዎች አንዱ እንደሚሆንም ይጠበቃል።

XS
SM
MD
LG