በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ውይይት በወቅታዊ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ቁመና


ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ፣ ዶ/ር ኢዮብ ተስፋዬ እና ዶ/ር ታደለ ፈረደ
ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ፣ ዶ/ር ኢዮብ ተስፋዬ እና ዶ/ር ታደለ ፈረደ

ይህ የውይይት ዝግጅት ወቅታዊና አጠቃላዩን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ይዞታን ይመለከታል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አስተዳደር ፣ የብልጽግና ወይም “የለውጥ ጊዜ” እየተባለ በሚጠራው የሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ፣ ኢኮኖሚው ያሳየውን ለውጥና አሁን የሚገኘበትን አጠቃላይ ቁመና የምንዳስበት ውይይት ነው፡፡ በለውጥ ሂደቱ የታዩ መሻሻሎችና መሰናክሎች፣ ከአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ትግበራው አንስቶ፣ ግዙፍና ጅምር ፕሮጀክቶችን በማስቀጠል፣ የአገርና የውጭ ንግድን ሚዛንን በመጠበቅ፣ የዋጋ ንረትንና ግሽበትን በማስተካከል፣ የፋይናንስ ሴክተሩን እንደገና በማቃናትና፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅት የመጣውን ድርብ ፈተና በመሻገር ረገድ እየታዩ ያሉ አፈጻጸሞችንና ሰሞኑን የተደረገውን የብር ኖቶች ለውጥም የምናይበት አግባብ ይኖራል፡፡ በዚህ ውይትት አብረውን የሚቆዩት ሶስት እንግዶቻቸን ሲሆኑ እነሱም፣ የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስቲር ደኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚስት ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዚዳንትና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚስት ምሁር ዶ/ር ታደለ ፈረደ እንዲሁም የማክሮ ኢኮኖሚስቱ ባለሙያ ዶ/ር ኢዮብ ተስፋዬ ናቸው፡፡

ውይይቱ በሶስት ክፍሎች እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ውይይት በወቅታዊ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ቁመና - ክፍል 1
please wait

No media source currently available

0:00 0:30:19 0:00
ውይይት በወቅታዊ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ቁመና - ክፍል 2
please wait

No media source currently available

0:00 0:32:44 0:00

ውይይት በወቅታዊ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ቁመና - ክፍል 3
please wait

No media source currently available

0:00 0:37:29 0:00

XS
SM
MD
LG