ዋሺንግተን ዲሲ —
መጤ ጠል የደርባን ከተማ ሰዎች /ደርባን ከተማ ማዘጋጃ ቤት ደጃፍ/
ደርባን ውስጥ ለጥቃት የተጋለጡ ኢትዮጵያዊያን ሰልፍ /መጋቢት 30/2007 ዓ.ም - ደርባን ከተማ ማዘጋጃ ቤት ደጃፍ/
በደቡብ አፍሪካይቱ ደርባን ከተማ ካለፈው ሣምንት ማብቂያ ጀምሮ በውጭ ሀገር ዜጎች ላይ በደረሱ ጥቃቶች ቢያንስ አምስት ሰው መገደሉን የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ትናንት፤ ማክሰኞ - ሚያዝያ 6 / 2007 ዓ.ም ደርባን ከተማ ጎዳናዎች ላይ ሁከት ተፈጥሯል።
ኢትዮጵያዊያኑን ጨምሮ ደርባን ውስጥ የሚኖሩ አፍሪካዊያን በፍርሃት ቤታቸውን ዘግተው ተቀምጠዋል።
ለዝርዝሩ የተያያዘውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡
-
ሔኖክ ሰማእግዜር