በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያና በኬንያ ድንበር የተደጋገመው የጎሣዎች ግጭት


ሞያሌዎቹ
ሞያሌዎቹ

በኢትዮጵያና በኬንያ የድንበር አካባቢዎች ከከትናንት በስተያው ቅዳሜ ወዲህ በተፈጠሩ የጎሣዎች ግጭቶች ቢያንስ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን አንድ የኬንያ ራዲዮ ጣቢያ ዘገበ፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:07:08 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በኢትዮጵያና በኬንያ የድንበር አካባቢዎች ከከትናንት በስተያው ቅዳሜ ወዲህ በተፈጠሩ የጎሣዎች ግጭቶች ቢያንስ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን አንድ የኬንያ ራዲዮ ጣቢያ ዘገበ፡፡

ካፒታል ኤፍኤም የሚባል አንድ ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ የሚያሠራጭ ራዲዮ ጣቢያ በከትናንት በስተያ - ዕሁድ ዜናው በኬንያና በኢትዮጵያ አዋሣኝ አካባቢዎች የሚኖሩት የቦረናና የገርባ ማኅበረሰቦች አባላት መጋጨታቸውን ተናግሯል፡፡

ሁለቱ ጎሣዎች ሞያሌ ውስጥ አዲስ ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ያስታወቁት የሃገር ውስጥ ጉዳይና የብሔራዊው መንግሥት ማስተባበሪያ ሚኒስቴር ዋና ፀሐፊ ሙቲያ ኢሪንጎ መሆናቸውንም ራዲዮ ጣቢያው አስታውቋል፡፡
ሞያሌዎቹ
ሞያሌዎቹ

ግጭቱ የተካሄደው በቦረናና በገርባ ጎሣዎች መካከል በኢትዮጵያና በኬንያ ድንበር ላይ መሆኑ ከመገለፁ በስተቀር ተገደሉ የተባሉት ወይም የተጎዱት ሰዎች የየትኛው ሃገር ዜጋ ስለመሆናቸው፣ በግጭቱ ውስጥ የኢትዮጵያ ወገን ሰዎች ተሣትፈው ይሁን አይሁን አልተገለፀም፡፡

የዛሬ ሁለት ሣምንትም በቱርካና አካባቢ ኢትዮጵያዊያኑ የሚሪሌ ጎሣ አባላት በኬንያ አሣ አስጋሪዎች ላይ አደረሱ በተባለ ጥቃት አሥር ሰው መገደሉን ናይሮቢ ስታንዳርድ ኦንላይን የሚባል የኢንተርኔት ዜና ማሠራጫ ዘግቧል፡፡

ስለሁኔታው ቪኦኤ ያነጋገራቸው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት የፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ጅሎ ቦኔታ ሁኔታውን ለማጣራት አንድ ቡድን ወደ ቱርካና አካባቢ መላኩን ገልፀዋል፡፡

የዛሬውን የሞያሌ ሁኔታ አስመልክቶ የኢትዮጵያን ወገን መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሣካም፡፡

ለተጨማሪና ዝርዝር መረጃ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG