አዲስ አበባ —
አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ዛሬ ዕሁድ፤ ሰኔ 9/2005 ዓ.ም በተደረገው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ግጥሚያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የደቡብ አፍሪካ አቻውን ሁለት ለአንድ በሆነ ግብ አሸነፈ፡፡
በዚህ ድልም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ደቡብ አፍሪካ፣ ቦትስዋና እና መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ የሚገኙበትን ምድብ በ13 ነጥብ በመምራት አንድ ግጥሚያ ቀርቶት ማጣሪያውን በመሪነት ማለፉን አረጋግጧል፡፡
መጭው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግጥሚያ ከመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ቡድን ጋር አንደሚሆን ታውቋል፡፡
በመጭው የአውሮፓዊያን 2014 ብራዚል ውስጥ ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ግብፅና አይቮሪ ኮስትን የመሣሰሉ ጠንካራ ቡድኖች ለተከታዩ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡
የዛሬውን ድል ተከትሎ የአዲስ አበባ ጎዳናዎች በፈንጠዝያና በፍንደቃ ማምሸታቸው ታውቋል፡፡
ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡