በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያዊያን አሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኦሮሚያ ሁኔታ ተሰለፉ

ቬርኔይ ትሪም - የዩናትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ዴስክ ኦፊሰር መልዕክታቸውን የያዘውን ደብዳቤ ከኢትዮጵያዊያኑ ሲቀበሉ - ሚያዝያ 29/2006 ዓ.ም፤ ዋሽንግተን
ቬርኔይ ትሪም - የዩናትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ዴስክ ኦፊሰር መልዕክታቸውን የያዘውን ደብዳቤ ከኢትዮጵያዊያኑ ሲቀበሉ - ሚያዝያ 29/2006 ዓ.ም፤ ዋሽንግተን

ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ ሰሞኑን ኦሮሚያ ውስጥ ሕይወት መጥፋቱን በመቃወም ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያ ሰልፈኞች ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደጅ ላይ ድምፃቸውን አሰምተዋል፡፡

ኢትዮጵያዊያን አሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኦሮሚያ ሁኔታ ተሰለፉ
ኢትዮጵያዊያን አሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኦሮሚያ ሁኔታ ተሰለፉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:30 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ ሰሞኑን ኦሮሚያ ውስጥ ሕይወት መጥፋቱን በመቃወም ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያ ሰልፈኞች ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደጅ ላይ ድምፃቸውን አሰምተዋል፡፡

የሰልፉ አዘጋጆች በያዙት መልዕክት “በአምቦና በሌሎችም የኦሮሚያ አካባቢዎች የተፈፀመውን ግድያ እንቃወማለን” የሚል ነው፡፡

ሰብዓዊነት የሚባል የመብቶች ተሟጋች ድርጅት እንዳስታወቀው በዋሽንግተን ዲ.ሲ. አካባቢ ያሉ ሲቪክ ማኅበራትና የፖለቲካ ድርጅቶች ባስተባበሩት በዚህ ሰልፍ ላይ “ጨቋኝ ነው” ያሉትን መንግሥት ኢትዮጵያዊያን በአንድነት እንዲታገሉ ጠይቀዋል፡፡

በሰልፉ ላይ ከአምቦ ከተማ አስተባባሪዎቹ በስልክ አግኝተናቸዋል ያሏቸው ሰው መልዕክታቸው በቀጥታ በአስተርጓሚ ለሰልፈኞቹ ተሰምቷል፤ ግጥሞች ተነብበዋል፡፡

በሰልፉ ጣልቃ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የኢትዮጵያ ዴስክ ኦፊሰር ቨርኔይ ትሪም ወጥተው የተሰብሳቢዎቹን የፅሁፍ መልዕክት ተቀብለዋል፡፡ በዚሁ ወቅት አስተባባሪዎቹ መልዕክታቸውን በቃልም አስተላልፈዋል፤ ቨርኔል ትሪምም በተፈጠረው ሁኔታ ማዘናቸውንና ኀዘናቸውንም ለሟቾች ቤተሰቦች መግለፃቸውን አመልክተው መልዕክቱን ለበላይ ባለሥልጣናት እንደሚያስተላልፉ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያዊያን በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
ኢትዮጵያዊያን በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

በተፈጠረው ሁኔታ ያዘነ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥትም ገልፆ ጉዳዩን መርምሮ ተጠያቂዎችን ለፍርድ እንደሚያቀርብ በተለያዩ አጋጣሚዎች መግለፁ ይታወቃል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG