ዋሽንግተን —
ሕጻናት የያዙ እናቶችና አዛውንቶች ጭምር የነበሩበት እጅግ የበዛ ቁጥር ያለው ሰላማዊ ሰልፈኛ ከማለዳው አንስቶ ነው “በዚያች አገር እየተካሄደ ነው” ያለውን ግድያ “በአፋጣኝ አስቁሙ!” እና “ለመንግስቱ የምትሰጡትንም እርዳታ አቋረጡ” የሚሉ ጥያቄዎችን ላቀረበላቸው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባለሥልጣናትና የምክር ቤት አባላት ሲያሰማ የዋለው።
ሳያቋርጥ ቀኑን በዘለቀው ካፊያ ውስጥ ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መሥሪያ ቤት ወደ በዋይት ሃውስ አልፎ ከምክር ቤት የሚያደርሱትን የከተማይቱን ጎዳናዎች ሞልቶ ሲሰማ የዋለውን ሰልፈኛ ድምጾች ያካተተውን ዘገባ ዝርዝር ከዚህ ይከታተሉ።