በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወጣቶች በምርጫው ምን መለወጥ ይፈልጋሉ? - በቪኦኤ የተካሄደ ክርክር


please wait

No media source currently available

0:00 0:34:57 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በመጭው ግንቦት ብሔራዊ ምርጫ “የኢትዮጵያ ሕዝብ በምን በምን ጉዳዮች ዙሪያ ለውጥ ይፈልጋል?” በሚል ጥያቄ ዙሪያ አራት ንቁ የፖለቲካ ተሣታፊ ወጣቶች በ”ለጥያቄዎ መልስ” ዝግጅታችን ላይ ቀርበዋል።

ሣራ ይስሃቅ ተክሉ የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ - ኢዴፓ አባል፤ ደስታ ዲንቃ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መድረክ አባልና የድርጅቱ የወጣቶች ዘርፍ መሪ፤ ኤልያስ ግደይ የገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ አባል፤ እንዲሁም ነፃና የፓርቲ አባል ያልሆነው አናኒያ ሶሪ በፕሮግራሙ ላይ ተሣትፈዋል።

ሰፊ ወደ ሆነው የሕዝቡ ጥያቄ ሳይገባ “የኢትዮጵያ ወጣቶች ምርጫው ምን ለውጥ እንዲያስገኝ ይመኛሉ?” ለሚል ነጥብ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊ የሆኑት የሥራ ዕድል፣ የትምህርት ጥራት፣ አሣታፊ የሆነ የፖለቲካ ሥርዓት፣ መልካም አስተዳደርን ጠቅሰዋል።

ሆኖም የኢትዮጵያ ወጣቶች የለውጥ ፍላጎት እንደ አካባቢአቸው አንግብጋቢ ጉዳይ ከክልል ክልል ወይም በገጠርና በከተማ እንደሚለያይ ተናግረዋል።

የኢህአደግን ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በመበተን ጠንካራ ተቃዋሚ እንዳይኖር በማድረግና አግላይ በመሆን ተችተዋል።

የኢህአዴግ አባል የሆነው ወጣት ኤልያስ ግደይ ኢትዮጵያ በልማታዊ ዴሞክራሲ ወደ ፍትሃዊ አስተዳደር እየተራመደች ያለች አገር ናት ብሏል።

ፈጥና ወደ ሊብራል ዴሞክራሲ እንዳትሸጋገር የሚያግዷትም ብዙ ችግሮች እንዳሉ የሕዝቡን ትምህርት ማነስ እንዲሁም የባህል ስብጥሩን እንደምሳሌ ጠቅሷል።

ለሙሉው ውይይትና ክርክር የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG