ከአገራቸው በልዩ ልዩ መንገድ ተሰደው፣ በሱዳንና በሊብያ አቋርጠው የወጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን በአሁኑ ወቅት ማልታ ውስጥ ይገኛሉ።
የተወሰኑት የፖለቲካ ጥገኝነት አግኝተው ከማልታ ወደ ሌላ አገር ለመሄድ እየተጠባበቁ ያሉ ሲሆን፤ ሌሎች በርካቶች ግን፣ ጥያቄያቸው ውድቅ ሆኖ እዚያው ማልታ ውስጥ ያለ ሥራ፣ በድንኳንና በዕቃ መጫኛ የብረት ሳጥን ማለትም ኮንቴነር ውስጥ ይኖራሉ። ከነዚህ መካከል ልጆች ያሏቸው መኖራቸውንም ተረድተናል።
ለመሆኑ እነዚህ ኢትዮጵያውያን እስከ መቼ ነው፤ ያለ ሥራ በባዕድ አገር የሚኖሩት? ወደ አገራቸው ለመመለስስ ችግር ይኖራቸው ይሆን? ከስደተኞቹና እዚያው ከማልታና ከኢትዮጵያ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ጋር የተካሄደ ቃለ ምልልስ ያድምጡ።