በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጠቅላይ ሚንስትሩ የፓርላማ ንግግር እና የኦነግ፣ የኦብነግ እና የግንቦት ሰባት ምላሽ


ዶ/ር አብይ አሕመድ /የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር/
ዶ/ር አብይ አሕመድ /የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር/

የትላንቱ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ በተለያዩ ወቅታዊ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ የፓርላማ ንግግር የብዙዎችን ቀልብ የሳበና አሁንም በማነጋገር ላይ ያለ ነው።

የጠቅላይ ሚንስትሩ የፓርላማ ንግግር እና - የኦነግ፣ የኦብነግ እና የአርበኞች-ግንቦት ሰባት ምላሽ
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:30 0:00

“ሕዝቡን ይቅርታ ጠይቀን፤ ይቅርታውም ተሰጥቶናል፤” ያሉትን የገዛ ድርጅታቸውን፣ ገዥውን ኢሐዲግን ተጠያቂ ያደረጉበትንና በትጥቅ ትግልየተሰማሩ ሦሥት ድርጅቶችን በአንጻሩ “ጦርነት ዋጋ የለውም” ሲሉ ተችተው ሃሳባችሁን ቀይሩ ባሉበት ላይ ከሚመለከታቸው ሁለቱን አግኝተናል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባሩን ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳን እና የኦጋዴን ነጻነት ግንባር የኮምዩኒኬሽን እና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባሉን አቶ ሃሰን አብዱላሂን በስልክ አነጋግረናል።

በጠቅላይ ሚንስትሩ ንግግር ስማቸው በምሳሌ የተነሳው ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የሚመሩት አርበኞች-ግንቦት ሰባት በበኩሉ ወደ ንግግሩ ዝርዝር ሳይገባ በሰጠው ምላሽ ይሁንታ መቀበሉን አመልክቶ፤ በሃገሪቱ እየተካሄደ ባለው የለውጥ እርምጃ ላይ የተነጣጠሩ ያላቸውን "የቅልበሳ ሙከራዎች በጥንቃቄ እየተከታተልኩ ነው፤” ብሏል።

የንቅናቄው ከፍተኛ አመራር በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ጉዳዮች ላይ እየመከረ መሆኑን ያመለከተው አርበኞጭ ግንቦት ሳባት አክሎም የሚደረስበትን በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG