በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባኤ ንግግር፤


Hailemariam D.
Hailemariam D.

የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ በመንግስታቱ ድርጅት ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ከሁለት ሺህ አስራ አምስት በሁዋላ ለሚኖረዉ የልማት አጀንዳ የዓለም አበይት ፈተናዎች በጋራ ለመጋፈጥ ነገር ግን የየራሳቸዉ ገጽታ ያላቸዉን ሃላፊነቶች መሰረት ያደረገ መተጋገዝም ለማጠናከር እንደሚረዳ ያላቸዉን እምነት ገልጸዋል።

ዓለም አሁን ያሉባትን እጂግ ከባድ ፍላጎቶች ለማሙዋላት አቅም ሃብር እንዳላት አስምረዉበታል።

አፍሪቃ በማደግ ላይ ያለች ለንግድና ለመዋእለ ንዋይ ምደባ ግዙፍ እድል የምትሰጥ አህጉር እንደሆነችና ኢትዮጵያን ጨምሮ ብዙዎቹ የአገሮች የሚሊኒዬሙን ግብ ለማስመዝገብ ዝግጁ መሆናቸዉን ተናግረዋል።

ሆኖም አፍሪቃ ለልማት ያላትን ጉጉት የከባቢ ዓዬር ለዉጥ ችግር እያደናቀፈ መሆኑን ጠቅሰዉ አፍሪቃ የችግሩ ምንጭ ባትሆንም የመፍትሔ አካል ናት በማለት፤ ስለ ታዳሽ ሃይል አስፈላጊነትም ተናግረዋል። የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር በዓለም ዙሪያ ባለፉት አስር ዓመታት ዉስጥ የታዮ የአመጽና የግጭት ሁኔታዎች ለልማት የሚደረጉ ጥረቶችን እንዲድበሰበሱ አድርገዋል ካሉ በሁዋላ በአሁኑ ጊዜ አመጽ በአፍሪቃ ሳይወሰን ዓለም አቀፋዊ ገጽታ እንደያዘ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፕሬዚደንት ኦባማ ጋር ያደረጉትን ግንኙነት ጭምር ዝርዝሩን ከዘገባዉ ያድምጡ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባኤ ያደረጉት ንግግር፤
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:26 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG