በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን ሁለት ወገኖችን የማቀራረብ ጥረት


ፎቶ - ፋይል
ፎቶ - ፋይል

በሃገር ውስጥና በውጭ ያሉትን ሁለቱን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስትያን ሲኖዶሶች ወደ አንድ ለማምጣት አዲስ ጥረት ተጀምሮ እየተካሄደ ነው።

ከዓለም አንጋፋ አብያተ ክርስትያን አንዷ የሆነችው የኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስትያን በዕድሜ ዘመኗ እጅግ የበዙ ፈተናዎችን ማለፏን ታሪኳ ይናገራል።

ባለፈው ሩብ ምዕት ዓመት በውስጧ የተፈጠረው መከፈልና በሃገር ውስጥና በውጭ በሚንቀሳቀሱ ሁለት ሲኖዶሶች መለያየት ብዙዎችን ሲያሳስብ የቀየ የራስ ምታት ሆኗል።

በሁለቱም ጎራ ያሉ አባቶችን ለማቀራረብና ወደ አንድነት ለመመለስ የተለያዩ ጥረቶች በተለያዩ ጊዜዎች ተደርገዋል።

የሰላምና የአንድነት ጉባዔ ሁለተኛ ዙር የሚባል የሁለቱም ወገኖች ተጠሪዎች ያሉበት ቡድን እነሆ አሁንም በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል።

ቡድኑ ከመላው ዓለም የተጠራሩ የቤተክርስትያኒቱ አባቶች የተካተቱበት ሃያ አራት አባላትና አሥራ ሁለት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ያሉት እንደሆነ መሪዎቹ ተናግረዋል።

አበረታች ምላሾችን ከሁለቱም አቅጣጫ እያገኘን ነው ይላሉ በጥረቱ ውስጥ ያሉ አሸማጋዮች

የቡድኑ ሰብሳቢ መላከ-ሕይወት ሃረገወይን ብርሃኑ የኢትዮጵያው ቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑ ቶሮንቶ ካናዳ የሚገኘው የደብረ-ገነት ቅዱስ ገብርዔል ቤተክርስትያን አገልጋይና በውጭው ቅዱስ ሲኖዶስ ሥር ያሉት የዋሺንግተን ዲሲው ደብረ-ኃይል ቅዱስ ገብርዔል ቤተክርስትያን አገልጋይ መምህር ፍሬሰው ከቪኦኤ ጋር ያደረጉትን ውይይት ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን ሁለት ወገኖች የማቀራረብ ጥረት
please wait

No media source currently available

0:00 0:29:46 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG