በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቆዳ ውጤቶች ንድፍ ባለሞያዋ ሩት 


የቆዳ ውጤቶች ንድፍ ባለሞያዋ ሩት 
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:40 0:00

የቆዳ ውጤቶች ንድፍ ባለሞያዋ ሩት 

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የቆዳ እና ሌጦ ምርት ቢኖራትም ከዘርፉ ብዙም ተጠቃሚ አይደለችም። ለዚህም ፈጠራ የታከለባቸው የቆዳ ምርቶችን ዲዛይን የሚነድፉ ተወዳዳሪ ባለሙያዎች በበቂ ደረጃ አለመኖራቸው አንዱ ምክንያት እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡

ሆኖም አሁን የዘርፉ ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ብቅ ብቅ እያሉ ነው። ሩት ግርማይ ከነዚህ አንዷ ናት።

በይበልጥ አፍሪካዊ እና ኢትዮጵያዊ ቀለም ያላቸውን መልዕክት አዘል ቦርሳዎች ዲዛይን በማድረግ ለገበያ ታቀርባለች፡፡

በአፍሪካ ደረጃ በተካሔዱ 2 ተከታታይ በቆዳ ውጤቶች ንድፍ (ዲዛይን) ውድድሮችን አሸንፋለች፡፡

ሩት ግርማይ ከአሜሪካ ድምጽ ጋራ የነበራትን ቆይታ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG