አዲስ አበባ - ዋሺንግተን ዲ.ሲ. —
ባለፈው ዓመት ብቻ 30 ሺህ የሚሆኑ ኢትየጵያዊያን በሕገወጥ አዘዋዋሪዎች ሥራ ፍለጋ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ እንደነጎዱ ዓለምአቀፉ የፍልሰት ድርጅት - አይኦኤም ገልጿል፡፡
ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ቤተሰቦች ንብረታቸውን በሕገወጥ ሁኔታ ድንበር ለሚያሻግሯቸው ወንጀለኛ ግለሰቦች ካስረከቡም በኋላ በየደረሱበት ዝርፊያና እንግልት እንደሚፈፀምባቸው፣ ሥራ የማያገኙበትም ሁኔታ እንዳለ በተደጋጋሚ ይሰማል፡፡
ኢትዮጵያዊያንን በሕጋዊ መንገድ ለሥራ ወደውጭ መላክን ዓላማው ያደረገው ወደ 350 አባል ድርጅቶች ያሉት የውጭ ሥራ ሥምሪት አገልግሎት ሰጭ ኤጀንሲ በሃገሪቱ ተመሥርቶ እየተንቀሣቀሰ ነው፡፡
የዚህ ማኅበር ሰብሳቢ አቶ መዝገቡ አሰፋ ይባላሉ፡፡ በአድማጮች ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡