በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ሰልፈኞች ጥያቄዎች


ከዋሽንግተን ዲሲና ከአካባቢው እንዲሁም ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የመጡ ኢትዮጵያውንና ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን በትላንትናው እለት ለዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ያቀረቧቸውን ጥያቄዎች ምንነትአብራሩ።

“ከፍተኛ የምዕራባውያን ረድኤት በማግኘት ከቀዳሚው አገሮች ተርታ የምትሰለፈው ኢትዮጵያ ባለፉት 25 ዓመታት የተቀበለችው ከአርባ ቢልዮን ዶላር የእርዳታ ገንዘብ ሕዝቦቿን ከድህነት ማጥ አላወጣም” ያሉት ትውልደ-ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያኑ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት ቃል፤ “መፍትሔው ሁሉንም አሳታፊ የፖለቲካ ሥርዓት መፈጠር ነው” ሲሉ ይከራከራሉ።

ሰልፉን ያስተባበሩትንና ደብዳቤውን በመፈረም የተሳተፉ ቡድኖች በመወከል ደብዳቤውን ለዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጽ/ቤት ከሰጡት ዶ/ር አክሎግ ቢራራ ጋር የተካሄደውን ቃለ ምልልስ ከዚህ ያድምጡ።

የኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ሰልፈኞች ጥያቄዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:22 0:00

የአሜሪካ ድምጽ የኢትዮጵያን መንግስት ምላሽ ለማግኘት ለዋሽንግተን ዲሲው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላቀረበው ጥያቄ በሰልፉ በቀጥታ የቀረበለት ጥያቄ ያለመኖሩን ጠቅሶ በአጠቃላይ በአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለሚቀርቡ ጥያቄዎችግን ወደፊት ተልዕኮው መልስ ሊሰጥ የሚችል መሆኑን አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG