በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቻይና አዲስ አበባ በረራ መስተጓጎል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 'ቦዪንግ 777-300ኢአር' አይሮፕላን
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 'ቦዪንግ 777-300ኢአር' አይሮፕላን

ከደቡባዊ ቻይናዪቱ ጓንዡ አይሮፕላን ጣቢያ ወደ አዲስ አበባ ለመብረር የተነሣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አይሮፕላን በመንገዱ ጣልቃ ሁለት ጊዜ ማረፉ ተገልጿል፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:03:14 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ከደቡባዊ ቻይናዪቱ ጓንዡ አይሮፕላን ጣቢያ ወደ አዲስ አበባ ለመብረር የተነሣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አይሮፕላን በመንገዱ ጣልቃ ሁለት ጊዜ ማረፉ ተገልጿል፡፡

ይህ ቀጥታ በረራ ማድረግ የነበረበት አይሮፕላን አንድ ጊዜ የሕንዷ ሙምባይ አይሮፕላን ጣቢያ ላይ ያረፈው ነዳጅ ለመቅዳት መሆኑንና ሁለተኛ ጊዜም ተመልሶ እዚያው ሙምባይ ያረፈው በሞተሩ ላይ ባጋጠመው እክል ምክንያት እንደሆነ ተዘግቧል፡፡

ይህ ቦዪንግ 777-300ኢአር የመንገደኞች አይሮፕላን በአጣዳፊ ምክንያት ቀደም ሲል በዕቅድ ውስጥ ባልተያዘ ሁኔታ ሁለት ጊዜ ይረፍ እንጂ አሣፍሯቸው የነበሩ 283 መንገደኞችና 14 የበረራ ቡድኑ አባላት በሠላም አዲስ አበባ መግባታቸው ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በደኅንነታቸው ስማቸው ከሚነሣ ማመላለሻዎች አንዱ እንደሆነ የሚነገር ሲሆን ስታር አላያንስ የሚባለው የታዋቂ አየር መንገዶች ኅብረት አባል እንደሆነም ይታወቃል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG