በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ግጭቶች ኢህአዲግ በጀመረው መንገድ ሊፈቱ አይችሉም” የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት


ግጭቶች ኢህአዲግ በጀመረው መንገድ ሊፈቱ አይችሉም ያሉ 16 ተቃዋሚ ፓርቲዎች የኃይል እርምጃ ከቀጠለ ነገሮች ሁሉ ከቁጥጥር ውጭ ሊሆኑ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።

ወቅታዊው ሁኔታውን መነሻ አድርገው የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት በሚል የተሰባሰቡት እነዚህ ፓርቲዎች የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ የፀጥታ ሀይሎች የሚፈጽሙትን ድብደባና ግድያ እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።

የፀጥታ ሀይሎች የተጋፈጡት ከታጠቁ ሰልፈኖች ጋር እንደሆነ መንግሥት በተደጋጋሚ አስታውቋል።

በኦሮምያና በአማራ ክልሎች የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች መጀመሩን ግጭቶች መፈጠራቸውን የበርካቶች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አቋማቸው ሲገልጹ መፍትሄ እንዲፈለግም ሲጠይቁ ቆይተዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

“ግጭቶች ኢህአዲግ በጀመረው መንገድ ሊፈቱ አይችሉም” የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:29 0:00

XS
SM
MD
LG