በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጋዜጠኞችን ጨምሮ ስምንት ሰዎች ታሠሩ


የታሠሩት ብሎገሮች /የፎቶ ምንጭ - ECADF ዌብሳይት/
የታሠሩት ብሎገሮች /የፎቶ ምንጭ - ECADF ዌብሳይት/

አዲስ አበባ ውስጥ ፖሊስ ከትናንት በስተያና ትናንት ስምንት ጋዜጠኞችና ብሎገሮችን በቁጥጥር ሥር አውሏል፡፡


ዞን-9
ዞን-9
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:37 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

አዲስ አበባ ውስጥ ፖሊስ ከትናንት በስተያና ትናንት ስምንት ጋዜጠኞችና ብሎገሮችን በቁጥጥር ሥር አውሏል፡፡

አብዛኞቹ ዞን-9 የሚባል ቡድን አባላት ናቸው ተብሏል፡፡

ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የታሠሩት ሰዎች ከቤተሰብም ሆነ ከወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር እንዳልተገናኙ የቅርብ ምንጮች አመልክተዋል፡፡

ከስምንቱ ታሣሪዎች ሰባቱ የተያዙት ዓርብ - ሚያዝያ 17/2006 ዓ.ም በተመሣሣይ ጊዜ ማለትም ከምሽቱ ወደ 11 ሰዓት ተኩል አካባቢ እንደነበረ ታሣሪዎቹን በቅርብ የሚያውቋቸው ምንጮች ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

የያንዳንዳቸው ቤት ተፈትሾ ካበቃ በኋላ ማዕከላዊ ወደሚባለው እሥር ቤት መወሰዳቸውን ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የታሠሩት ብሎገሮች /የፎቶ ምንጭ - ECADF ዌብሳይት/
የታሠሩት ብሎገሮች /የፎቶ ምንጭ - ECADF ዌብሳይት/
XS
SM
MD
LG