አዲስ አበባ —
ላለፉት 13 ቀናት በማእከላዊ የወንጀል ምርመራ ጣቢያ ያለምንም ግንኙነት ታስረው ከቆዩት ጋዜጠኞችና የዞን 9 ጦማር ጸሃፊዎች መካከል ስድስቱ ታሣሪዎች ዛሬ፤ ረቡዕ፣ ሚያዝያ 29/2014 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀረቡ።
ፖሊስ በሽብር ወንጀል መጠርጠሩን ገልፆ የአሥር ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቆ ፍርድ ቤቱ ፈቅዶለታል።
የኅቡዕ ድርጅቶች አባል መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ ያስታወቀው ፖሊስ ገና ያልተያዙ ግብረ አበሮቻቸውን እያፈላለግሁኝ ነው ብሏል።
የጋዜጠኞቹና ፀሀፊዎቹ ይዞታ እንዳሳሰባቸው ዓለም አቀፍ የመብቶች ተሟጋች ድርጅቶችና መንግሥታት ተቃውሞ በማሰማት ላይ ናቸው።
ለተጨማሪ መለስካቸው አምሃ በአራዳ ፍርድ ቤት ዝግ ችሎቱን ከውጭ ሆኖ ተከታትሎ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።