ብዙ ሙስሊሞች መንግሥት በምርጫዎቹ ጣልቃ እየገባ ነው ብለው እንደሚያምኑ ከአዲስ አበባ ይሰማል፡፡
የተቃውሞው ትዕይንት የተካሄደው በአዲስ አበባና በሌሎችም ከተሞች መሆኑ የተሰማ ሲሆን በአዲስ አበባው አንዋር መስጊድ የተገኙት በብዙ ሺሆች የሚቆጠሩ ሠልፈኞች ቢጫ ካርድ ይዘው “ድምፃችን ይሰማ”፤ “ዋ! ዋ!” ይሉ ነበር፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ምርጫው የሚፈፀመው በሙስሊሙ ኅብረተሰብ ዕውቅና ባልተሰጣቸው ሰዎች ነው በሚል እንዲታገድላቸው ፍርድ ቤትን ለመጠየቅ የሞከሩ የሙስሊሙ ኅብረተሰብ ቅሬታዎች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ጠበቃ አቤቱታቸውን ፍርድ ቤት እንደማይቀበል አስታውቀዋል፡፡
የኮሚቴው አባላት የሚገኙት በእሥር ላይ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
የቪኦኤ ዘጋቢዎችን ሪፖርቶች ያዳምጡ፡፡