በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደጋን ወሎ ውስጥ ከፖሊስ ጋር በተፈጠረ ግጭት ሕይወት ጠፋ


ወሎ/ ኢትዮጵያ
ወሎ/ ኢትዮጵያ

ወሎ፤ ቃሉ ወረዳ ደጋን ከተማ ውስጥ፣ በነዋሪው ሕዝብና በፌዴራል ፖሊስ መካከል ግጭት መፈጠሩ ተገለፀ።


please wait

No media source currently available

0:00 0:06:07 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


ግጭቱን የቀሰቀሰው በፖሊሶች የታሠረ አንድ የወጣቶች ተወካይ በሕዝብ ትብብር እንዲለቀቅ ከተደረገ በኋላ ነው ሲሉ አንድ የዐይን ምስክር ነኝ ያሉ ሰው ለቪኦኤ አመልክተዋል፡፡

አቡበከር የተባለ የደጋን ወጣት ትናንት ዕሁድ በፖሊሶች ተይዞ ወደ ገርባ ከተወሰደ በኋላ ነዋሪው ሕዝብ እቦታው ድረስ በመሄድ አስለቅቆታል ብለዋል እማኙ። የፖሊስ ክፍሉን ማብራሪያ ለማግኘት ያደግነው ጥረት ለጊዜው አልተሣካም፡፡ ሙከራችንን እንቀጥላለን፡፡

በሌላ በኩል ግን ሁኔታውን አስመልክቶ ለሮይተርስ የዜና አውታር መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ የኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሺመልስ ከማል “አጋጣሚው የተፈጠረው በገርባ ከተማ ለትናንት ዕሁድ ተላልፎ የነበረው የእሥልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምርጫ እየተካሄደ ሣለ አንድ የተቃወመ ግለሰብ የድምፅ አሰጣጡን ሂደት ለመረበሽ ሲሞክር በቁጥጥር ሥር በመዋሉ ነው” ብለዋል፡፡

አቶ ሽመልስ አክለውም “ደጋፊዎቹ ግለሰቦች ከፖሊስ ቁጥጥር በኃይል ሊያስለቅቁ የሞከሩት ቆንጨራና ሽጉጦች ወይም ጠብመንጃዎችን ይዘው ነበር” ብለዋል፡፡ “የአክራሪው ቡድን አባላት” ያሏቸው ሦስት ሰዎች እሥር ቤቱን በኃይል ሰብረው ለመግባት ሲሞክሩ ፖሊሶቹ ተኩሰው ገድለዋቸዋል” ሲሉም አቶ ሺመልስ ከማል አክለዋል፡፡

በግጭቱ ውስጥ አንድ ፖሊስ መገደሉንና ሌሎች ሁለት ፖሊሶች መቁሰላቸውንም አቶ ሽመልስ ተናግረዋል፡፡

ነዋሪዎቹ እሥረኛውን እንዴት አስለቀቁት? ለምንስ ታሰረ? ምን ተፈጠረ?
XS
SM
MD
LG