በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፋር ክልል ሆስፒታሎችና የጤና ማዕከላት በጦርነት በመውደማቸው ህብረተሰቡ ለጤና ችግር ተጋልጧል


በአፋር ክልል ሆስፒታሎችና የጤና ማዕከላት በጦርነት በመውደማቸው ህብረተሰቡ ለጤና ችግር ተጋልጧል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:22 0:00

በመቶዎች የሚቆጠሩ ሆስፒቷሎቿና የጤና ማዕከላቷ በጦርነት በወደመባት አፋር ክልል ያሉ ባለሥልጣናት፣ የህክምና ባለሙያዎች፣ እንዲሁም ነዋሪዎች ክልሉ አሳሳቢ የጤና ችግር ስለተጋረጠበት አስቸኳይ ዕርዳታ ያስፈልገናል ሲሉ ጠይቀዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ በመላው ዓለም ያለው አጠቃላይ ቀውስ እየተባባሰ በመሆኑ ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን ድጋፍ አስቸጋሪ አድርጎታል።

ባለፈው ግንቦት ህፃን ልጅዋ ከመሬት ላይ ያገኘችውን ነገር አንስታ ከዋጠች በኋላ በመሞቷ፣ ሜርያም አብደላ አሊ ልቧ ተሰብሯል።

“ወደ ሆስፒታል ብንወስዳትም መሳሪያ ስለሌለን ኦፕራሲዎን ማድረግ አንችልም ወደ ሰመራ ከተማ ውሰዷት እሉን። በመንገድ ላይ ሳለን ሞተች” ብላለች ሜሪያም።

ሜርያም አብደላ አሊ ነዋሪነቷ የትግራይ ሰራዊት እስከ አለፈው መጋቢት ተቁጣጣሯት በነበረችውና፣ የጤና ተቋማቷን አውድሞ በሄደባት የበርሃሌ ከተማ ነው።

የአፋር ክልል መንግሥት እንደሚለው 60 የሚሆኑ የጤና ማዕከላት በትግራይ ሰራዊት ወድመዋል። የትግራይ ክልል መንግሥትና የትግራይ ሰራዊት ክሱን አይቀበሉም።

ሜርያም አብደላ አሊ ልጇን በወሰደችበት የበርሃሌ ህክምና ማዕከል የሚሰራው ዶ/ር መሃመድ ሁሴን አብደላ የሜሪያምን ልጅ ለማትረፍ የሚያስችላቸው የህክምና መሳሪያ እንደሌላቸው ይናገራል።

“ይህ የጤና ማዕከል የህክምና መሳሪያዎች ከሚገኙባቸው ማዕከላት እንዱ ነበር። ባለፉት ግዜያት አስፈላጊ የሆኑት መሳሪያዎችና መድሃኒቶች በመኖራቸው ኦፕራሲዮን ማድረግ እንችል ነበር። ህወሓት ይህን ጤና ተቋም ሙሉ ለሙሉ አውድሞታል” ይላሉ ዶ/ር መሃመድ ሁሴን አብደላ።

በአፋር የደረሰውን ውድመት በተመለከተ፣ ቪኦኤ በትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ህወሓት) በኩል አስተያየት ለማግኘት ጠይቆ መልስ አላገኘም።

ከበርሃሌ አቅራቢያ በምትገኘው ኮናባ አውራጃ እንድ የጤና ማዕከል ተዘርፎና ወድሞ ይታያል።

“የህክምና ላብራቶሪዎች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፤ ኤድስንና የስኳር በሽታን ጨምሮ ምርመራ ማድረግ አንችልም፤ ምክንያቱም መሳሪያዎች የሉንም። ከፍተኛ የመድሃኒት እጥረት ችግር አለ። የመብራት አለመኖርም ችግር ፈጥሯል” ብለዋል የኮናባ ጤና ማዕከል ሃላፊ ከድር ደሬሳ ሁመድ።

በዜና ማሰራጫዎች ተደጋጋሚ ርዕስ ሆኖ የሚቀርበው በኢትዮጵያ ስላለው የምግብ ዕርዳታ አስፈላጊነት ቢሆንም፤ ባለሥልጣናት እንደሚሉት ግን ከፍተኛ የሆነ የህክምና አገልግሎት ፍላጉትም አለ።

የተመድ የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው፣ በትግራይ ሰራዊት ተይዘው በነበሩት የአፋር ክልል ከተሞች ለህይወት አስጊ የሆነ የህክምና አገልግሎት እጥረት አለ።

የዓለም ጤና ድርጅት ለቪኦኤ እንዳስታወቀው፣ በኢትዮጵያ የሚደረገው ዕርዳታ ውጤታማ እንዲሆን፣ የምግብ ዕርዳታ ከህክምና ዕርዳታ ጋር አብሮ መሰጠት አለበት።

“አስፈላጊ የሆኑ አቅርቦቶችንም ሆነ፣ ለተላላፊ በሽተኞች የሚሰጥን ምግብ የተመለከተም ይሁን፣ ወይም ደግሞ ለህጻናት ክትባትም ሆነ ለእናቶችና ህፃናት የሚሰጡ አገልግሎቶችን በተመለከተ፤ እነዚህ አግልግሎቶች ሲሰጡ ከምግብ ጋር መሰጠታቸው በጣም አስፈላጊ ነው” ብለዋል በዓለም ጤና ድርጅት አማካሪ የሆኑት ዶ/ር ኢልሃም አብደላይ ኑር።

ለሜርያም አብደላ አሊ ዕርዳታ የደረሰው ዘግይቶና ልጇን ካጣች በኋላ ነው። ሌሎችን ለማዳን ግን አሁንም ግዜ አለ።

XS
SM
MD
LG