በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ልዩ ውይይት:- በኢትዮጵያ ሰሞንኛ ጉዳዮች


የኢትዮጵያ ካርታ
የኢትዮጵያ ካርታ

“ኢትዮጵያ የሚያማታ መንገድ ላይ እንዳለች በግልጽ ያሳያል። የመጀመሪያው መፍትሔ የሚሆነው የቆየውን የዓመታት ጥያቄ መፍታት ነው። ይሄ ለሃገሪቷም ሥልጣን ላይ ላለውም ፓርቲ ለሌሎችም ስለ ኢትዮጵያ ለሚቆረቆሩ ሁሉ እስትንፋስ የሚሰጥ ነው።” ዶ/ር አሰግድ ሃብተወልድ የሥራ አመራር ሥልጠና ባለ ሞያ ከዋሽንግተን ዲሲ።

የውይይቱን ሁለተኛ ክፍል ከዚህ ያድምጡ፡

ልዩ ውይይት:- በኢትዮጵያ ሰሞንኛ ጉዳዮች( ሁለተኛ ክፍል)
please wait

No media source currently available

0:00 0:19:10 0:00

“በእኔ በኩል አሁን መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች:- በሰለማዊ ሰልፎች ላይ መተኮስና ማንገላታትመቆም አለበት።ማናቸውንም የትግል መንገድ በመጠቀም መብታቸውን ለማስከበር ሲታገሉ የታሰሩ የፖለቲካ መሪዎችም ሆኑጋዜጠኞችና ሌሎች መፈታት አለባቸው። “እኛ ብቻ ነን” ሳይባል ተቃዋሚ ወገኖችን ጨምሮ ከመንግስት ውጭ ያሉትንሰዎች የሚያሳትፍ ውይይት በአስቸኳይ መከፈት አለበት” ፕሮፌሰር ተሾመ አበበ በምሥራቃዊ ኢሊኖይ ክፍለ ግዛትዩኒቨርሲቲ፥ ቻርልስተን የምጣኔ ሃብት ጥናት መምሕር።

በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች እየታየ ያለውን ሕዝባዊ አመጽ ምንነት ለመተንተን፤ ቀጣዩን አቅጣጫና ሁነኛየመፍትሔ አማራጮች ለመመርመር የሚጥር ልዩ ልዩ ባለሞያዎችና የኢትዮጵያ ጉዳይ አዋቂዎች የሚሳተፉበት ልዩተከታታይ ውይይት አካል ነው።

ተወያዮቹ:- ፕሮፌሰር ተሾመ አበበ በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ ምሥራቃዊ ኢሊኖይ ክፍለ ግዛት ዩኒቨርሲቲ፥ ቻርልስተንየምጣኔ ሃብት ጥናት መምሕር እና የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ አስተዳዳሪ ሲሆኑ፤ ዶ.ር አሰግድ ሃብተወልድ በዋሽንግተንናአጎራባች ግዛቶች በሥራ አመራር ሞያና የሌሎች ልዩልዩ ክህሎቶች ማበልጸጊያ ዘዴዎች አሰልጣኝ ናቸው።

አሳሳቢውና ሁነኛ መላ የሚሹ አንገብጋቢ የአገርና የሕዝብ ጉዳዮች፤ አሁንም እያነጋገሩ ነው።

የፕሮግራሙ ተከታታዮችም በያላችሁበት ትወያዩባቸው ዘንድ እየጋበዝን የየበኩላችሁን ገንቢ ይዘት የተላበሱ ሃሳቦችበመላክ ጭምር ትሳተፉ ዘንድ እናበረታታለን።

የውይይቱን የመጀመሪያ ክፍል ከዚህ ያድምጡ፤

ልዩ ውይይት:- በኢትዮጵያ ሰሞንኛ ጉዳዮች
please wait

No media source currently available

0:00 0:19:04 0:00

XS
SM
MD
LG