በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች የሚገኙ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፤ በሀገሪቱ የሚታየው የጸጥታ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ስጋት ካደረባቸው ቆይቷል፤ በአሁኑ ወቅት፤ ስጋቱ በተለይ በመቱ ዩኒቨርስቲ የመማር ማስተማር ሂደትን አስተጓጉሏል።
ከትግራይ ክልል የመጡ ከ100 የሚበልጡ ተማሪዎች ድህንነታችን አደጋ ላይ ወድቋል ሲሉ ትምህርት ቤቱን ለቀው ወደ ጋምቤላ ክልል ተጉዘዋል። የጸጥታ ሃይሎች ወደ ግቢው መግባታቸው ስጋት የፈጠረባቸው የኦሮሚያ ክልል ተወላጆችም እንዲሁ ትምህርት ቤቱን ለቀው ወጥተዋል።
ከሌሎች ክልል የመጡ ተማሪዎችም እንዲሁ ተሰባስበው፤ የመማር ማስተማር ሂደቱ ካልተጀመረና፤ ጸጥታ ካልተጠበቀ፤ ወደ ትውልድ ቀያችን እንመለሳለን ብለዋል።
የመቱ ዩኒቨርስቲ ባለስልጣናትም የተፈጠረው ሁኔታ የመማር ማስተማር ሂደቱን ማስተጓጎሉን ገልጸው፤ ማክሰኞለት ትምህርት እንዲጀመር አዘው ነበር፤ ማምሻውን እንደተረዳንው በርካታ ተማሪዎች ወደ ክፍል ከመግባት ይልቅ፤ ወደ አገራችን መልሱን እያሉ ነው።
የመቱ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝደንት ዶር ታደሰ ሀብታሙ፤ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ