በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ልጆች በኢትዮጵያ - ትናንት፣ ዛሬና ነገ


በኢትዮጵያ ሕፃናት የዛሬ ይዞታ ላይ አዲስ ሪፖርት ወጣ፡፡

ያሻቀበው የገንዘብ ግሽበት መጠን፣ የወጣቶች ሥራ አጥነት መብዛትና የሕፃናት መብቶች ጥበቃ የተደራጀ አሠራር አለመኖር ብዙ ሕፃናት የሙሉ መብቶቻቸው ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ያገዳቸው መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥትና የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት ጉዳዮች ድርጅት በጋራ ያወጡት በሕፃናት መብቶች ላይ ያተኮረ ሪፖርት አስታውቋል፡፡

ይህ “በኢትዮጵያ ለወንድ ልጆችና ለሴት ልጆች ትኩረት መስጠት፤ ትናንት፣ ዛሬና ነገ” በሚል ርዕስ የወጣው ሪፖርት ለሕፃናት “አንዳች መልካም ዜና ሰንቋል” ይላል ዘገባው፡፡

በ1990 ዓ.ም (እአአ) - የዛሬ ሃያ ዓመት ማለት ነው፤ ዕድሜአቸው ከ5 ዓመት በታች ከሆነ አንድ ሺህ ሕፃናት 200 ይሞቱ ነበር፡፡ ይህ ግዙፍ ቁጥር ላለፉት አምስት ዓመታት ወደ 90 አሽቆልቁሏል፡፡

ባለፉት ሰባት ዓመታት ውስጥ 7500 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተጨምረዋል፡፡የማኅበረሰብ የማገገሚያ ምግብ መስጫ ማዕከላት ቁጥር ከ200 ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ወደ 10 ሺህ ማደጉ የብዙ ሕፃናትን ሕይወት ከጥፋት አትርፏል፡፡

ሪፖርቱ “የአቅም ክፍተቶች” ሲል የፈረጃቸውን ችግሮችም ይዘረዝራል፡፡

ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG