በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ በየዓመቱ 2 ሚሊዮን ሥራ ፈላጊዎች ገበያውን ይቀላቀላሉ


በኢትዮጵያ በየዓመቱ 2 ሚሊዮን ሥራ ፈላጊዎች ገበያውን ይቀላቀላሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:41 0:00

በኢትዮጵያ በየዓመቱ ሁለት ሚሊዮን ዐዲስ ሥራ ፈላጊዎች ገበያውን እንደሚቀላቀሉ፣ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

እነዚኽን ሥራ ፈላጊዎች ታሳቢ በማድረግ፣ ሀገራዊ የሥራ ፈጠራ ዕቅድ መዘጋጀቱንና በየዓመቱ ለሦስት ሚሊዮን ሰዎች ሥራ ለመፍጠር መታቀዱን፣ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ንጉሡ ጥላሁን ገልጸዋል፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ወጣቶች፣ “ከዩኒቨርሲቲዎች ከተመረቅን በኋላ፣ ሥራ ማግኘት ትልቅ ፈተና ኾኖብናል፤” ይላሉ፡፡ መንግሥት ለችግራቸው መፍትሔ እንዲሰጣቸውም ጠይቀዋል፡፡

የዐዲስ አበባ ንግድ እና ዘርፍ ማኅበራት በበኩሉ፣ ለወጣቶች የሥራ ፈጠራ አስተዋፅኦ የሚያደርግ የቢዝነስ ማበልጸጊያ ማዕከል ማቋቋሙን ይፋ አድርጓል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

XS
SM
MD
LG