የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ አጀማመር፥ የዛሬ ይዞታና መጪ ሁኔታ በተከታታይ ውይይቶች የምንመለከታቸው ጭብጦች ናቸው።
የኢትዮጵያ ኅገ መንግስት ስለ ጋዜጠኝነት ምን ይላል? የጸረ ሽብር ኅጉ አንድምታ?
መሠረታዊን የሰው ልጆች የንግግር ነጻነት የሚመለከቱ ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች ጨምሮ የአገሪቱን ኅጎች ትርጓሜና ምንነት እንመረምራለን።
ባለ ሁለት ክፍሉ ቀዳሚ ዝግጅት የውይይቱን መጨረሻ አካቷል።
ከአንጋፋና ከወጣት ጋዜጠኞች፥ እንዲሁም ከፈቃድ ሰጪና ተቆጣጣሪው የመንግስት መሥሪያ ቤት ባለ ሥልጣናት ጋር በተከታታይ የሚካሄዱ ቀጣይ ውይይቶች በአንጻሩ የወቅቱን የአገሪቱን የብዙኃን መገናኛዎች ይዞታና መጪውን አቅጣጫ ለማመላከት ይጥራሉ።