ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጋራ በተያያዘ፣ ከፌደራል እና ከክልል ተቋማት የመንግሥት ሥራቸው የታገዱ፣ ከአንድ ሺሕ በላይ የትግራይ ተወላጅ የፖሊስ አባላት ወደ መደበኛ ቦታቸው እንዳልተመለሱ፣ ኢትዮጵያዊ የመብቶች ተሟጋች ተቋም፣ሂዩማን ራይትስ ፈርስት አስታወቀ፡፡
የመብቶች ተሟጋች ድርጅቱ፣ የፖሊስ አባላቱ ከነቤተሰቦቻቸው ለልዩ ልዩ ችግሮች እና ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንደተዳረጉ አውስቶ፣ የፌደራሉ መንግሥት እና ክልላዊ አስተዳደሮች፣ በፕሪቶርያው ስምምነት መሠረት ወደ መደበኛ ሥራቸው እንዲመልሷቸው ጥሪ አቅርቧል፡፡
በሪፖርቱ ላይ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት፣ የድርጅቱ ምክትል ዲሬክተር አቶ መብርሂ ብርሃነ፣ መንግሥት ለጥሪው አዎንታዊ ምላሽ ካልሰጠ፣ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስዱት አመልክተዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም