አዲስ አበባ —
እንዲከራከሩ ብይን የተሰጣቸው የሕግ ድንጋጌ እንዲለወጥ ታዘዘ፤ በሙስና የተከሰሱ ጉዳይም ታይቷል፡፡
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ አራተኛ ወንጀል ችሎት በሽብር አድራጎት ተከስሰው ከነበሩት የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጥያቄዎች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትና ሌሎች ተከሣሾች መካከል አሥር ሰዎችና ሁለት ድርጅቶች መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ አሰናበተ፡፡
ሌሎቹን ተከሣሾች የተከሰሱባቸው የሕግ ድንጋጌዎች ተለውጠው እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል፡፡
15ኛ ወንጀል ችሎት ደግሞ በሙስና ወንጀል የተከሰሱትን የአቶ መላኩ ፈንታን ጉዳይ “የሚያየው ፍርድ ቤት የቱ ነው” በሚለው ጥያቄ ላይ የመጨረሻውን ውሣኔ ለማሰማት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ከነአቶ መላኩ ፈንታ ጋር የተከሰሱት የቀድሞ የሃገር ውስጥ ደኅንነት ኃላፊ ተጨማሪ ክሦች ቀርበውባቸዋል፡፡
መለስካቸው አምሃ የዛሬን የፍርድ ቤት ውሎ ዝርዝር ዘገባ ይዟል፡፡