በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከእስር እንዲፈቱ ስምምነት ላይ ተደረሰ ተባለ


የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በሱዳን ጉብኝታቸው ከፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ጋራ ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ያደረጉትን ውይይት በተመለከተ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለምን አነጋግረናል።

የሱዳንን ወደብ በጋራ ለማልማትና ለማስተዳደር ፣ በአባይ ወንዝ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ዙሪያ በጋራ ለመሥራትናድንበር አካባቢ ነፃ የንግድ እንቀስቃሴ እንዲኖር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

በተጨማሪም በሱዳን እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንዲፈቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ያቀረቡትንም ጥያቄ ፕሬዚዳንት አልበሽር ተቀብለዋል ተብሏል።

ጽዮን ግርማ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለምን በጉዳዩ ዙሪያ አነጋግራለች።

በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከእስር እንዲፈቱ ስምምነት ላይ ተደረሰ ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:32 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG