“የአገር ጉዳይ”... ተመልሶ መጥቷል። የአንድ አገርና ሕዝብ ፈተናዎች፥ የመውጫ መንገዶችና ተሥፋ።
ትላንትናችንን፥ ዛሬንና ነገን፤ መንታ መንገድ ላይ ያለች በምትመስለው ሃገር ሰሞንኛ ይዞታ ውስጥ የሚደረግ የሃሳብ ቅኝት ነው። ራዲዮ መጽሔት ከዚህ ቀደም ይህን መሰል ሁኔታ ሲፈጠር በተለየ ትኩረት ያሰልስ እንዳደረገው ሁሉ ዛሬም አነጋጋሪ፥ አሳሳቢና ሁነኛ መላ ለሚሹት አንገብጋቢ የአገርና የሕዝብ ጉዳዮች ገጾቹን ገልጧል።
በኢትዮጵያ ጉዳዮች የሚጽፉ፥ በተለያዩ መንገዶች በንቃት የሚሳተፉና በሚጠበቡባቸው የሞያ መስኮች ለብዙዎች ጥቅም የሚውሉ ሥራዎቻቸው የሚታወቁ፤ የሕዝብ ጉዳይ ግድ የሚላቸውን የማኅበረሰብ አባላት ማነጋገሩን ቀጥለናል።
በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ባተኮሩ ምሁራዊ ጽሁፎቹ በሥፋት የሚታወቀውና መንፈሳዊ ይዘት ያላቸው በርካታ መጽሃፍት ደራሲው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እና በፖለቲካ ተሳፎው ሳቢያ ለበረታ እንግልት ቢዳረግም ዛሬም ከኢትዮጵያ ጉዳዮች ያልራቀው
የቀድሞው የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው ለውይይቱ ተሰይመዋል።
እርሶም የዚህ ተከታታይ ውይይት ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ተጋብዘዋል። አድማጮች በያላችሁበት ከምታደርጉት ውይይት በተጨማሪ ለአገርና ለሕዝብ ይበጃሉ የምትሏቸውን አዎንታዊ ሃሳቦች አድርሱን።
ውይይቱን ከዚህ ያድምጡ፤
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ