በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአገር ጉዳይ:- የነገይቱ ኢትዮጵያ በሦሥት የተቃዋሚ ድርጅቶች ተጠሪዎች ዓይን


ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፥ አቶ የሺ ዋስ አሰፋ እና አቶ ግደይ ዘርዓ-ጽዮን
ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፥ አቶ የሺ ዋስ አሰፋ እና አቶ ግደይ ዘርዓ-ጽዮን

“.. ከዚህ በኋላ ከክላሽ ወደ ካርድ እንቀይረው የሥርዓት መለወጫ መንገዳችንን።” አቶ የሺ ዋስ አሰፋ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር። “ችግሩን መዘርዘር ብቻ ሳይሆን፣ መፍትሔውስ ምን መሆን አለበት? የሚለው ጥያቄ ነው ዋናው ነገር።” አቶ ግደይ ዘርዓ-ጽዮን የኢትጵያ ሕዝብ ብሔራዊ ሸንጎ ጸሃፊ። “የመጀመሪያው ድርድር ሆነ፥ ምን ሆነ፣ መዳረሻው ምንድ ነው? ነው፤ መጀመሪያ ምን ለማድረግ ነው የምንፈልገው?” ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የአርበኞች-ግንቦት 7 ሊቀመንበር

(1) የአገር ጉዳይ:- የነገይቱ ኢትዮጵያ የሃሳብ መንገዶች - ክፍል አንድ
please wait

No media source currently available

0:00 0:14:21 0:00
(2) የአገር ጉዳይ:- የነገይቱ ኢትዮጵያ የሃሳብ መንገዶች - ክፍል ሁለት
please wait

No media source currently available

0:00 0:17:14 0:00
(3) የአገር ጉዳይ:- የነገይቱ ኢትዮጵያ የሃሳብ መንገዶች - ክፍል ሦሥት
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:43 0:00

የነገይቱ ኢትዮጵያ በሦሥት የተቃዋሚ ድርጅቶች ዓይን ሲቃኝ።

የአገር ጉዳይ በተሰኘው ልዩ የራዲዮ መጽሔት ተከታታይ ፕሮግራም አገሪቱ በገባችበት የፖለቲካ ቀውስ እና በጊዜው ጥያቄዎች ዙሪያ የተወያዩ የሦሥት የተቃዋሚ ድርጅቶች ተጠሪዎች የነገውን አቅጣጫዎች አስመልክቶም የእኛ የሚሉትን ሃሳብ ይፈነጥቃሉ።

ለመሆኑ ምን ዓይነት ለውጥ? እንዴት? የሚሉትን ነጥቦች በውይይታቸው ይፈትሻሉ።

ተወያዮች:- ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የአርበኞች-ግንቦት 7 ሊቀመንበር እና የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ምክር ቤት የጋራ ሊቀመንበር፤

አቶ ግደይ ዘርዓ-ጽዮን የኢትጵያ ሕዝብ ብሔራዊ ሸንጎ ጸሃፊ እና እንዲሁም፣ አቶ የሺ ዋስ አሰፋ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ናቸው።

ከገዢው ኢሕአዴግ በተለይም ደግሞ ሰሞንኑን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አመራርና አባላት ሹም ሽር ካደረገው የሕዝባዊ ወያኔ አርነት ትግራይ - ሕወአት ባለ ሥልጣናት ተጠሪዎች ለመጋበዝ ያደረግነው ጥረት ግን ለጊዜው አልተሳካም። ቃል በገቡበት መሠረት እንደተገኙ አነጋግረን እናቀርባለን።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG