“አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ያገራችንን ችግር እያባባሰ ነው። እናም መነሳት አለበት።” ሲል የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግሬስ - ኦፌኮ ዛሬ ምጅክሰኞ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ አሳሰበ።
“መፍትሄው ውይይት እና ድርድር እንጅ የኃይል እርምጃ አይደለም፤” ሲል ኦፌኮ በአገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ይሰፍን ዘንድ በመንግስት ሊወስዱ ይገባል፤ ያላቸውን እርምጃዎችም ዘርዝሯል።
የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግሬስ ኦፌኮ የሰጠውን መገለጫ ተንተርሶ የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግሬስ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ በቀለ ገርባ ጋር የተካሄደውን ቃለ ምልልስ ከዚህ ያድምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ