በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሳምንታዊ የስፖርት ዝግጅት


sport Logo
sport Logo

ቻይና ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ ለአሥር ቀናት የሚቆየውን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ታስተናግዳለች። በዚህ አሥራ አምስተኛው የዓለም ሻምፒዮና ውድድር ላይ ከሚሳተፉ 61 አትሌቶች መካከል የመጀመሪያው ቡድን አባላት ትላንት እሁድ ተሸኝተዋል።

ቻይና ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ ለአሥር ቀናት የሚቆየውን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ታስተናግዳለች። በዚህ አሥራ አምስተኛው የዓለም ሻምፒዮና ውድድር ላይ ከሚሳተፉ 61 አትሌቶች መካከል የመጀመሪያው ቡድን አባላት ትላንት እሁድ ተሸኝተዋል። ቅዳሜ በመክፈቻው እለት የሚካሄደውን የማራቶን ሩጫ ጨምሮ፥ የኢትዮጵያ አትሌቶች በተለያዩ የመካከለኛና ረዥም ርቀት ውድድሮች የወርቅ ሜዳልያ ሊያገኙ እንደሚችሉ ከወዲሁ እየተነገረ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፥ በቤይጂንጉ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ማግስት ዙሪክ ላይ በሚካሄደው ዳያመንድ ሊግ፥ በቅርቡ በሺህ አምስት መቶ አዲስ የዓለም ክብረወሰን ያስመዘገበችው አትሊት ገንዘቤ ዲባባ፥ በሦስት ሺህ ትሮጣለች። ካሸነፈች፥ የሊጉን ዋንጫ እንደምትወስድ ተዘግቧል።

ሳምንታዊ የስፖርት ዝግጅት
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:05 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG