በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፖለቲካ ልዩነት ተፈጥሮ አስከፊ በሆነ መንገድ ብንለያይም አቶ መለስ በዚህ ዕድሜ ህይወቱ በማለፉ በጣም አዝናለሁ - ስየ አብርሃ


Ethiopia's Prime Minister Meles Zenawi, September 17, 2011.
Ethiopia's Prime Minister Meles Zenawi, September 17, 2011.

“ወቅቱ የኢህአዲግ ደጋፊ፣ የኢህአዲግ ተቃዋሚ፣ የዚህ ብሔር የዚያ ብሔር፣ የዚህ ሃይማኖት የዚያ ሃይማኖት ተከታይ ሳንባባል ፊታችን ወደተደቀነው ሁኔታ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ፣ በመቻቻልና በዕርቅ መንፈስ የምንጓዝበት መሆን ይገባዋል” ሲሉ የሀገሪቱ የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ስየ አብርሃ አሣሰቡ።

አቶ ስየ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ዜና ዕረፍት አስመልክቶ ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ በሰጡት አስተያየት ኢትዮጵያ የያዘቻቸው ጥሩ ጥሩ የልማት ጅማሮዎች በመልካም አስተዳደር፣ በመቻቻልና ሁሉን ባካተተ መንገድ ወደፊት መግፋት እንዲቻል መክረዋል፡፡

“የፖለቲካ መደላድሉ አስቸጋሪና አሳሳቢ ከመሆኑ አኳያ አቶ መለስ ይህን በበቂ መደላድል አስተካክለውት በሆነ እንዴት በተደሰትን የሚል ሁኔታ ላይ እንገኛለን” ብለዋል።

“ኢህአዴግም የአቶ መለስን ከውስጡ መጉደል እንደፖለቲካ ለውጥ ተጠቅሞ የኢትዮጵያን ሕዝብ ጥያቄና ተስፋ የሚመልስበት” አድርጎ ቢወስደው እንደሚመኙ ገልጠዋል።

በኢህአዲግ በኩል ሕዝቡን ለበጎ መንፈስ ለማነሳሳት እና ለማስተባበር፣ በሕዝብ ላይ ብዙ ጉዳት ያስከተሉ የፀረ-ሽብርና የሲቪክ ማህበራትን የሚመለከተው ህጎች እንዲሠረዙ፣ ከዚህ ጋር ተያይዞም የታሠሩ እንዲፈቱ፣ ክስ የተመሠረተባቸውም እንዲነሣላቸው ማድረግ በጎ ተግባር ነው ብለዋል።

ተቃዋሚዎችም ከቁጣና ከጥላቻ በመቆጠብ ስለለዕርቅና ስለፍቅር፣ ስለአንድነት ማሰብና መናገር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG