በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ንግግሩ እንደቀጠለ ነው፤ ሌሎችም የዛሬ ውሎ ጉዳዮች


ንግግሩ እንደቀጠለ ነው፤ ሌሎችም የዛሬ ውሎ ጉዳዮች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:54 0:00

በኢትዮጵያ መንግሥትና በህወሓት መካከል ባለፈው ሣምንት የተጀመረው የሠላም ድርድር ዛሬም ቀጥሎ ውሏል።

ትናንት፤ ዕሁድ ይጠናቀቃል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ንግግር በእስከ አሁኑ ቆይታው ምን ላይ እንደደረሰ ግን ከየትኛውም ወገን የተባለ ነገር የለም።

በተፋላሚዎቹ ወገኖች መካከል ያለው መካሰስ የቀጠለ ሲሆን “ፌዴራሉ መንግሥት የትግራይ ክልልን የሚያስተዳድር ከትግራይ ተወላጆች ውጭ የሆነ ምስለኔ አስተዳደር ለመሾም ተዘጋጅቷል” ሲሉ የህወሓት ጦር ዋና አዛዥ ያቀረቡትን ክሥ መንግሥቱ ያስተባበለ ሲሆን ሠራዊቱ ወደያዛቸው አካባቢዎች ዕርዳታ መላክ መጀመሩንም ገልጿል።

XS
SM
MD
LG