የመከላከያ ኃይሎቹ ሽረን፣ አላማጣንና ኮረምን የያዙት “በከተሞች ውስጥ ጦርነት ሳያካሂዱ” ነው ሲል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ አገልግሎት ዛሬ አስታውቋል።
የፌዴራል መንግሥቱ ኃይሎች ሽረን ትናንት መቆጣጠራቸውን ያረጋገጠውና በበኩሉ የክተት ጥሪ ያወጣው ህወሓት የተኩስ አቁም ሥምምነት በአስቸኳይ እንዲደረግና ወደ ክልሉ ሰብዓዊ ድጋፍ ያለምንም ገደብ እንዲቀርብም ጠይቋል።
ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆም ከዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ እየቀረቡ ላሉ ጥሪዎችን በግልፅ ምላሽ ያልሰጠው ፌዴራሉ መንግሥት “ሠራዊቱ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች እርዳታ በተሣለጠ ሁኔታ እንዲደርስ በቂ ዝግጅት አድርጌአለሁ” ብሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ጦርነቱ እንዲቆምና የሰላም ንግግር እንዲጀመር ከዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ የሚሰሙት ግፊቶች እንደቀጠሉ ነው።
[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]