በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ከኢትዮጵያ መንግሥትና ከህወሓት ባለሥልጣናት ጋር ተነጋገሩ


የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ከኢትዮጵያ መንግሥትና ከህወሓት ባለሥልጣናት ጋር ተነጋገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:45 0:00

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሃመር ከኢትዮጵያ መንግሥት እና ከህወሓት ባለሥልጣናት ጋር መወያየታቸውን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አስታወቋል።

ባለፈው ሰኞ ኢትዮጵያ የገቡት የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሃመር፣ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንደዚሁም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጋር ጦርነቱ በአስቸኳይ መቆም እንዳለበት እና በአፍሪካ ህብረት መሪነት ወደ ሰላም ድርድር ማምራት እንደሚያስፈልግ መወያያታቸውን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታውቋል።

የዩናይትድ ስቴትሱ ልዩ ልዑክ ለህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤልም ተመሳሳይ መልዕክት ማስተላለፋቸውን አመልክቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት ለችግር በተጋለጡ ሰዎች ላይ እና በሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ላይ ተጽእኖ እያሳደረ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገልጿል፡፡

ወደ ትግራይ ክልል በየብስም ይሁን በአየር የሚደረገው የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት መቋረጡን የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል የኤርትራ ጦር ወደ ጦርነቱ ገብቷል በሚል የሚወጡ መረጃዎችን በተመለከተ አስተያየት የሰጡት በብሪታንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ፣ ድንበሩን የተቆጣጠረው የሕወሓት ኃይል በመሆኑ፣ “በአሁኑ ጊዜ ከኤርትራ ጋር በድንበር ላይ ለሚፈጠረው ነገር ተጠያቂ አይደለንም” ብለዋል።

ኤርትራ በተለያዩ ግንባሮች በትግራይ ክልል ላይ ጥቃት እየፈጸመች ነው በሚል ሕወሓት የከሰሰ ሲሆን ከኤርትራ በኩል ለዚህ ክስ እስካሁን ቀጥተኛ ምላሽ አልተሰጠም፡፡

XS
SM
MD
LG