በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ተወቀሰች


የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባወጣው ዓመታዊ የሰብዓዊ መብቶች ሪፖርቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እንደሚፈጸሙ አስታወቀ። ኢትዮጵያ ሪፖርቱን የሀሰት ስትል ውድቅ አደረገች።

መሥሪያ ቤቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም አገሮች የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ዓመታዊ ሪፖርት ይፋ ያደረገው፥ መጋቢት 30 ቀን 2003 ዓ ም ነው።

በዚሁ ከ 50 ገጾች በላይ ባለው ሪፖርቱ እንዳተተው፥ ባለፈው የአውሮፓውያኑ ዓመት መንግሥትና የፀጥታ ኃይሎች ከፖለቲካ ጋር በተዛመደ ግድያ ለመፈጸማቸው ማረጋገጫ ባይኖርም፥ ወታደሮች ሱማሌ ክልል ውስጥ ባለው ሁከት ሳቢያ ግድያዎችና ግድያዎችና ሌሎች የመብት ጥሰቶችን ለመፈጸማቸው አስተማማኝ ሪፖርቶች አሉ ብሏል።

አሁንም ከፖለቲካ ጋር በተያያዘ ስለ ሰዎች የደረሱበት መጥፋት ዘገባዎች ባይኖሩም ያካባቢ ፖሊሶች፥ የሚሊሺያ አባሎችና የብሄራዊ ደህንነትና የፀጥታ አገልግሎት ሠራተኞት ግለሰቦችን በተለይም የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ ቀስቃሾችን ከማንም ጋር እንዳይገናኙ በማድረግ፥ ይዘው ስለማሠራቸው ቁጥር ሥፍር የሌላቸው ሪፖርቶች መኖራቸውን የስቴት ዲፓርትመንቱ ሪፖርት ያትታል።

ዛሬ በኢትዮጵያ ከ 120 በላይ በሚሆኑ ወህኒ ቤቶች 86 ሺህ ሰዎች በእሥር ላይ እንደሚገኙ ከነዚህ ውስጥ 2, 474ቱ ሴቶች 546ቱ ደግሞ ከእናቶቻቸው ጋር አብረው የታሠሩ ሕጻናት መሆናቸውን አብራርቷል።

የተቃዋሚው የአንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀ መንበር ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሣ ባለፈው ጥቅምት ከእሥር በምህረት መፈታታቸውንም አስፍሯል።

የሀገሪቱ ሕገ-መንግሥት በኢትዮጵያ የመናገርና የፕሬስ ነፃነት መኖሩን ቢደነግግም መንግሥቱ በተግባር እንደማያከብራቸው ግን ገልጿል።

ቀጣዩ «ዴሞክራሲ በተግባር» ፕሮግራም መሥሪያ ቤቱ በኢትዮጵያ ላይ ያወጣውን ሪፖርት ባጭሩ ይመለከታል። የኢትዮጵያ መንግሥት ለሪፖርቱ የሰጠውን ምላሽ ይዟል።

ዝርዝሩን ያድምጡ

XS
SM
MD
LG