አንጋፋው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ከሥራ መታገዳቸውን አስታውቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን፣ ኹለቱን የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች ያገደው “ገለልተኛ አይደላችሁም፣ ከዓላማ ውጭም ተንቀሳቅሳችኋል” በሚል እና ተያያዥ ምክንያቶች መኾኑን በጻፈላቸው ደብዳቤ አመልክቷል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ዋና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገመቹ እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ያሬድ ኃይለማርያም ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት ድርጅቶቻቸው ላይ የቀረበውን ውንጀላ አስተባብለዋል፡፡
ከባለሥልጣኑ አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡
የኹለቱን ድርጅቶች ዕግድ ተከትሎ፣ ከሰሞኑ የታገዱ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ቁጥር 4 ደርሷል፡፡
መድረክ / ፎረም