በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ልዩ ኀይልን ወደ ጸጥታ ተቋማት መልሶ የማደራጀት የመንግሥት ፕሮግራም ተቃውሞ ገጠመው


ልዩ ኀይልን ወደ ጸጥታ ተቋማት መልሶ የማደራጀት የመንግሥት ፕሮግራም ተቃውሞ ገጠመው
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:50 0:00

መንግሥት፣ የአማራ ክልል ልዩ ኃይልን በዳግም አደረጃጀት ወደ ሌሎች የጸጥታ ተቋማት ለማስገባት እየወሰደ ያለው ርምጃ፣ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ተቃውሞ እየገጠመው ነው።

በዛሬው ዕለት፣ በሰሜን ወሎ እና በምዕራብ ጎንደር በርካታ ስፍራዎች፣ ኅብረተሰቡ መንገድ በመዝጋት፣ የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ እና ጎማ በማቃጠል፣ ቁጣውን ሲገልጽ መዋሉን ከእነዚኹ አካባቢዎች አስተያየት የሰጡን ግለሰቦች ገልጸዋል፡፡

በትላንትናው ዕለት፣ በወልዲያ አካባቢ በመከላከያ ሠራዊት እና በልዩ ኃይል አባላት መሀከል በነበረ የተኩስ ልውውጥ፣ አንድ ሕይወቱ ያለፈና ሌላ አንድ ቁስለኛ ወደ ከተማዋ ሆስፒተል ገብተዋል፤ ሲል፣ ማንነቱ እንዳይጠቀስ የፈለገ የሕክምና ባለሞያ ተናግሯል፡፡

ልዩ ልዩ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ አፈጻጸሙን በመቃወም መግለጫ አውጥተዋል፡፡ ከፓርቲዎቹ አንዱ የኾኑት፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) እና የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች በሰጡን አስተያየት፣ ርምጃው፥ ግልጽነት እንደሚጎድለውና ሌሎች ችግሮችን ሊያስከትል እንደሚችል ያላቸውን ስጋት አስታውቀዋል፡፡

የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ ሰላማዊት ካሳ በበኩላቸው፣ ርምጃው፣ በኹሉም ክልሎች በተመሳሳይ ጊዜ በመከናወን ላይ ነው፤ ሲሉ፣ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG