በቀይ ሽብር ዘመቻ ወቅት በበርካታ ሰዎች ግድያ “እጃቸው አለበት” በሚል የተጠረጠሩትን ኢትዮጵያዊ ጉዳይ ዘ ሄግ ላይ ያስቻለው ችሎት በአራተኛ ቀኑ የበደሉ ሰለባ ሞሆናቸውን የተናገሩ ወገኖችን ሰምቷል።
“በደርግ አባልነቴ ሰለባ ለሆኑት ሰዎች፥ በእነርሱም አማካኝነት ለመላው ኢትዮጵያውያን ተንበርክኬ ይቅርታ እጠይቃለሁ” ያሉትን የኔዘርላንድ ዜግነት ያላቸውን የቀድሞ የደርግ አባል የስልሳ ሶት ዓመቱ የቀድሞ የደርግ አባል አቶ እሸቱን የእምነት-ክህደት ቃል ሰምቷል።
አቶ እሸቱ በ1970ዎቹ መጀመሪያ ዓመታት በጎጃም ክፍለ ሃገር በደብረ ማርቆስ ከተማ “ተፈጽሟል” ከተባለውና 75 ወጣቶች ከተገደሉበት ወንጀል ጋር በተዛመደ የተለያዩ የቴክኒክ እና የዓይን እማኞች ማስረጃዎች ቢቀርብባቸውም “የያዛችሁት የተሳሳተ ሰው ነው” የሚለውን የማስተባበያ አቋማቸውን ግን አልለወጡም።
በእስር ላይ ሳሉ “ከፍተኛ” ስቃይና እንግልት ቢደርስባቸውም ከሞት እጣ ለመትረፍ የበቁትና የቤተሰብ አባሎቻቸው የተገደሉባቸው ሌሎች በሃሙሱ የችሎቱ ውሎ በጊዜው “ደርሶብናል” ያሉትን በደል አቅርበዋል።
ከሰባቱ ምስክሮች ሦሥቱን በችሎቱ ውሎ መገባደጂያ ከዚያው ከዘሄግ በስልክ አነጋግረናል።
ሙሉ ቃለ ምልልሱን ከዚህ ያድምጡ።
በችሎቱ የምስክርነት ቃላቸውን ከመስጠታቸው አስቀድሞ ከአቶ አብረሃም ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ ከዚህ ያድምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ